4 ከብር ዝገትን አስወግድ፤ ከዚያ በኋላ አንጥረኛ ያሳምረዋል።
4 ከብር ዝገትን አስወግድ፤ አንጥረኛውም ንጹሕ ነገር ያገኛል፤
4 ከብር ዝገትን አስወግድ፥ ፈጽሞም ይጠራል።
“የሰው ልጅ ሆይ! እስራኤላውያን ለእኔ ምንም አይጠቅሙኝም፤ እነርሱ ለእኔ ብር በእሳት ከነጠረ በኋላ ዝቃጩ እንደሚቀር የመዳብ፥ የቆርቆሮ፥ የብረትና የእርሳስ ዝቃጭ ናቸው።
ወርቅና ብር በእሳት እንደሚፈተን እግዚአብሔርም የሰውን ልብ ይፈትናል።
ይህ ፈተና የሚደርስባችሁ የእምነታችሁን እውነተኛነት ለማረጋገጥ ነው፤ የሚጠፋ ወርቅ እንኳ በእሳት ይፈተናል፤ ከወርቅ ይልቅ የከበረ እምነታችሁ እንደዚሁ መፈተን አለበት፤ ይህም የተፈተነ እምነታችሁ ኢየሱስ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ ምስጋናን፥ ክብርንና ውዳሴን ያስገኝላችኋል።
ንጉሥ የሚያስበውን ማወቅ አትችልም፤ የንጉሥ አሳብ እንደ ሰማይ የመጠቀ እንደ ውቅያኖስ የጠለቀ ነው።
በልቡ ክፋት እያለ በአንደበቱ ልዝብ ቃል የሚናገር ሰው ውጪው በሚያምር በብር ቀለም እንደ ተቀባ የሸክላ ዕቃ ነው።
አምላክ ሆይ! ብር በእሳት ተፈትኖ እንደሚጠራ ፈተንከን።