Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 48:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 እንደ ብር ሳይሆን በመከራ እሳት አንጥሬአችኋለሁ፥ በችግር እቶንም ፈትኜአችኋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 እነሆ፤ እንደ ብር ባይሆንም አንጥሬሃለሁ፤ በመከራ እቶን ፈትኜሃለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 እነሆ፥ አንጥሬሃለሁ ነገር ግን እንደ ብር አይደለም፤ በመከራም እቶን ፈትኜሃለሁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 እነሆ፥ ለወ​ጥ​ሁህ፤ ነገር ግን በብር አይ​ደ​ለም፤ ከመ​ከ​ራም እቶን አው​ጥ​ቼ​ሃ​ለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 እነሆ፥ አንጥሬሃለሁ ነገር ግን እንደ ብር አይደለም፥ በመከራም እቶን ፈትኜሃለሁ።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 48:10
18 Referencias Cruzadas  

እነርሱ እኮ እንደ እቶን እሳት ከምታቃጥል ከግብጽ ምድር ያወጣሃቸው ሕዝብህ ናቸው።


እርሱ እርምጃዬን ሁሉ ያውቃል፤ ቢፈትነኝም እንደ ወርቅ ንጹሕ ሆኜ ያገኘኛል።


“በእውነቱ ማዕድን ተቈፍሮ ብር የሚወጣበትና ወርቅ የሚጣራበት ቦታ አለ።


አምላክ ሆይ! ብር በእሳት ተፈትኖ እንደሚጠራ ፈተንከን።


ወርቅና ብር በእሳት እንደሚፈተን እግዚአብሔርም የሰውን ልብ ይፈትናል።


እንግዲህ የያዕቆብ ልጆች እስራኤላውያን ለኃጢአታቸው ይቅርታ ማግኘት የሚችሉት የአሕዛብን የመሠዊያ ድንጋዮች እንደ ኖራ ፈጭተው፥ የዕጣን መሠዊያዎችንም ሆነ አሼራ ተብላ የምትጠራውን የሴት አምላክ ምስሎች ሲያስወግዱ ነው።


ይህ ቃል ኪዳን እንደ ጋለ ምድጃ ከሆነችባቸው አገር ከግብጽ ባወጣኋቸው ጊዜ ለቀድሞ አባቶቻችሁ የሰጠሁት ነው፤ ለእኔ እንዲታዘዙና እኔ የምላቸውን ሁሉ እንዲፈጽሙ ነገርኳቸው፤ የሚታዘዙኝም ከሆነ እነርሱ ሕዝቤ እንደሚሆኑና እኔም አምላካቸው እንደምሆን ገለጥኩላቸው።


ከዚህም የተነሣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሕዝቤን ለማጥራት እንደ ብረት እፈትናቸዋለሁ፤ ሕዝቤ ክፉ ነገር ስለ ፈጸሙ ይህን ከማድረግ በቀር ሌላ ምን አደርጋቸዋለሁ?


ዐመፀኞችንና የበደሉኝን ከመካከላችሁ አስወግዳለሁ፤ አሁን ከሚኖሩባቸው አገሮች አወጣቸዋለሁ፤ ነገር ግን ወደ እስራኤል ምድር እንዲመለሱ ከቶ አልፈቅድላቸውም፤ በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።”


እናንተ ግን እሳት እንደሚነድበት የብረት ምድጃ ከሆነችው ከግብጽ መንጥቆ እግዚአብሔር ያወጣችሁ ዛሬ እንደ ሆናችሁት ሁሉ ለራሱ የተለያችሁ ወገኖቹ እንድትሆኑ ነው።


ይህ ፈተና የሚደርስባችሁ የእምነታችሁን እውነተኛነት ለማረጋገጥ ነው፤ የሚጠፋ ወርቅ እንኳ በእሳት ይፈተናል፤ ከወርቅ ይልቅ የከበረ እምነታችሁ እንደዚሁ መፈተን አለበት፤ ይህም የተፈተነ እምነታችሁ ኢየሱስ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ ምስጋናን፥ ክብርንና ውዳሴን ያስገኝላችኋል።


ወዳጆች ሆይ! እንደ እሳት በሚፈትን መከራ ውስጥ ስትገኙ ያልተለመደ እንግዳ ነገር እንደ ደረሰባችሁ አድርጋችሁ አትደነቁ፤


እኔ የምወዳቸውን ሁሉ እገሥጻቸዋለሁ፤ እቀጣቸዋለሁም፤ ስለዚህ ትጋ፤ ንስሓም ግባ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos