መዝሙር 63:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰው መልካም ምግብ በልቶ እንደሚጠግብ ነፍሴ በአንተ ትረካለች፤ ስለዚህ የምስጋና መዝሙር በደስታ እዘምርልሃለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነፍሴ በቅቤና በሥብ እንደሚረካ ሰው ትረካለች፤ አፌም በሚያዜሙ ከንፈሮች በደስታ ያወድስሃል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህ በሕይወቴ ዘመን አመሰግንሃለሁ፥ በአንተም ስም እጆቼን አነሣለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለእነርሱ ለራሳቸው ክፉ ነገርን አጸኑ፤ ወጥመድን ይሰውሩ ዘንድ ተማከሩ፤ የሚያምንም የለም ይላሉ። |
አምላክ ሆይ! ከዚያም በኋላ ለአንተ ለምታስደስተኝ ወደ መሠዊያህ ሄጄ እሰግድልሃለሁ፤ አንተ አምላኬ ነህ፤ በገናዬን እየደረደርኩ አመሰግንሃለሁ።
አንተ የመረጥካቸውና በተቀደሰ አደባባይህ እንዲኖሩ ወደ ራስህ ያቀረብካቸው፥ ደስ ይበላቸው፤ እኛም ከቤትህ በሚገኘው መልካም ነገርና ከመቅደስህ በሚገኘው በረከት እንረካለን።
እጄን ይዘህ ሳበኝ፤ አብረን እንሩጥ። ንጉሡ ወደ እልፍኙ አስገባኝ፤ በዚያም አብረን ደስ ይለናል፤ ፍቅርህ ከወይን ጠጅ ይልቅ ያስደስታል፤ ስለዚህ ቈነጃጅት ሁሉ እጅግ ያፈቅሩሃል።
የሠራዊት አምላክ በዚህች በጽዮን ተራራ ለዓለም ሕዝቦች ሁሉ ታላቅ ግብዣ ያዘጋጃል፤ በግብዣውም ላይ ምርጥ የወይን ጠጅና፥ የተሟላ ምግብ ይዘጋጃል።