መዝሙር 59:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዴት እንደ ሸመቁብኝ ተመልከት! እግዚአብሔር ሆይ! ምንም በደልና ኃጢአት ሳልሠራ ዐመፀኞች ሰዎች በእኔ ላይ ያሤራሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነሆ በነፍሴ ላይ አድብተዋልና፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ ጨካኞች ያለ በደሌ፣ ያለ ኀጢአቴ በላዬ ተሰብስበው ዶለቱብኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከግፍ አድራጊዎች ታደገኝ፥ ከደም ሰዎችም አድነኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለሕዝብህ ጭንቅን አሳየሃቸው፥ አስደንጋጩንም ወይን አጠጣኸን። |
ከምድሪቱ ላይ ታማኝ ሰው ጠፍቶአል፤ አንድም ትክክለኛ ሰው የለም፤ ሁላቸውም ሰውን ለመግደል ያደባሉ፤ እርስ በርሳቸውም አንዱ ሌላውን ተከታትሎ ያጠምዳል።
ነገር ግን እሺ አትበላቸው፤ እርሱን ሳንገድል እህል አንበላም፤ ውሃም አንጠጣም በማለት የተማማሉ ከአርባ የሚበልጡ ሰዎች እርሱን ለመግደል አድፍጠዋል፤ አሁን እነርሱ የሚጠብቁት የአንተን መልስ ብቻ ነው።”
ሳኦል ዳዊትን ሊገድለው ማቀዱን ለልጁ ለዮናታንና ባለሟሎቹ ለሆኑት ባለሥልጣኖች ሁሉ ነገረ፤ ነገር ግን ዮናታን ዳዊትን እጅግ ይወደው ነበር።
አባቴ ሆይ! እነሆ፥ ከካባህ ላይ ቈርጬ የያዝኩትን ጨርቅ ተመልከት! ታዲያ እኮ ልገድልህ እችል ነበር፤ ነገር ግን ይህን በማድረግ ፈንታ የልብስህን ጫፍ ቈረጥሁ፤ በአንተ ላይ ለማመፅም ሆነ ወይም በአንተ ላይ ጒዳት ላደርስብህ አለመፈለጌን በዚህ መረዳት ትችላለህ፤ አንተ ግን ምንም ነገር ሳላደርግና ሳልበድልህ እኔን ለመግደል ትከታተለኛለህ።
ከዚያም በኋላ ዳዊትን እንዲህ አለው፤ “አንተ እውነተኛ ሰው ነህ! እኔ ግን ስሕተተኛ ነኝ፤ ይህን የመሰለ በደል ስፈጽምብህ አንተ ለእኔ ቸርነት አድርገህልኛል!