ሞገደኞች አደጋ ሊጥሉብኝ ተነሡ፤ ጨካኞች ሊገድሉኝ ይፈልጋሉ፤ ስለ እግዚአብሔርም አያስቡም።
ባዕዳን ተነሥተውብኛልና፤ ግፈኞች ነፍሴን ሽተዋታል፤ እግዚአብሔርንም ከምንም አልቈጠሩም። ሴላ
አቤቱ፥ በስምህ አድነኝ፥ በኃይልህም ፍረድልኝ።
ከጠላት ድምፅ፥ ከኀጢአተኛም ማሠቃየት የተነሣ፥ ዐመፃን በላዬ መልሰውብኛልና፥ ሊያጠፉኝም ተነሥተውብኛልና።
ዘወትር እግዚአብሔርን አስቀድማለሁ፤ እርሱም በቀኜ ስለ ሆነ አልታወከም።
ከመቅደሱ ርዳታውን ይላክልህ፤ ከጽዮን ተራራም ይደግፍህ።
ክፉ ሰዎች እንደ ውሻ ስብስብ ከበቡኝ፤ እጆቼንና እግሮቼን ቸነከሩ።
ክፉ ሰው ሁልጊዜ በልቡ ክፋትን ያስባል፤ እግዚአብሔርን ከቶ አይፈራም፤ አያከብረውምም።
ሊገድሉኝ የሚፈልጉ ሁሉ ይፈሩ፤ ግራም ይጋቡ። የእኔን ጒዳት የሚመኙ ሁሉ ኀፍረት ይድረስባቸው።
አምላክ ሆይ! ፍረድልኝ፤ በአንተ ከማያምኑ አሕዛብ ፊት ስለ እኔ ተከራከርልኝ፤ ከአታላዮችና ከክፉ ሰዎችም እጅ አድነኝ።
እግዚአብሔር “ክፉ አድራጊዎች ከቶ አያስተውሉምን? ሰዎች እንጀራን እንደሚበሉ ክፉ አድራጊዎች ሕዝቤን ይበዘብዛሉ፤ እነርሱም ወደ እኔ ወደ እግዚአብሔር አይጸልዩም።” ይላል።
በወንድሞቼ መካከል እንግዳ፥ በእናቴም ልጆች መካከል ባይተዋር ሆንኩ።
አምላክ ሆይ! ትዕቢተኞች በእኔ ላይ ተነሥተዋል፤ አንተን የማይፈሩ ጨካኞች ሰዎች ሊገድሉኝ ይፈልጋሉ።
ይህንንም የሚያደርጉት አብንም ሆነ እኔን ስላላወቁ ነው።