መዝሙር 50:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የምስጋና መሥዋዕት ለእግዚአብሔር አቅርብ፤ ስእለትህንም ለልዑል ስጥ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ለእግዚአብሔር የምስጋና መሥዋዕት አቅርብ፤ ለልዑልም ስእለትህን ስጥ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለእግዚአብሔር የምስጋናን መሥዋዕት ሠዋ፥ ለልዑልም ስእለትህን ስጥ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የመድኀኒቴ አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፥ ከደም አድነኝ፥ አንደበቴም በአንተ ጽድቅ ደስ ይለዋል። |
አሁን ግን በከበቡኝ ጠላቶቼ ላይ ራሴን ከፍ አደረግሁ፤ በደስታ “እልል” እያልኩ በመቅደሱ ውስጥ መሥዋዕት አቀርባለሁ፤ እየዘመርኩም እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ።
የኑዛዜ ቃል ይዛችሁ ወደ እግዚአብሔር ተመለሱ፤ እንዲህም በሉት፦ “ኃጢአታችንን ሁሉ ይቅር በለን፤ በምሕረት ተቀበለን፤ እኛም የአንደበታችን መልካም ፍሬ የሆነውን ምስጋና እናቀርብልሃለን።
እነሆ መልካም ዜናን የሚያበሥር፥ ሰላምንም የሚያውጅ መልእክተኛ በተራሮች ላይ እየመጣ ነው። የይሁዳ ሕዝብ ሆይ! ክፉዎች ጠላቶችህ ፈጽሞ ስለ ተደመሰሱ ከእንግዲህ ወዲህ አገርህን ከቶ አይወሩአትም! ስለዚህ ዓመት በዓሎችህን በደስታ አክብር! ስእለትህንም ለእግዚአብሔር ስጥ!
ነነዌ ሆይ! አደጋ ጣይ መጥቶብሻል! ስለዚህ ምሽጎችሽን አጠናክሪ! አውራ መንገዱን ሁሉ ጠብቂ! ወገብሽን ታጠቂ! ኀይልሽንም ሁሉ አጠናክሪ!
እንግዲህ ወንድሞቼ ሆይ! እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ፥ ሕያውና የተቀደሰ መሥዋዕት አድርጋችሁ ሁለንተናችሁን እንድታቀርቡ በመሐሪው በእግዚአብሔር ስም እለምናችኋለሁ፤ ይህም ማቅረብ የሚገባችሁ ቅንነት ያለው እውነተኛ የእግዚአብሔር አገልግሎት ነው።
“ለእግዚአብሔር አምላክህ ስእለት በምታደርግበት ጊዜ ለመስጠት ወይም ለመፈጸም ቃል የገባህበትን ስእለት አታዘግይ፤ እግዚአብሔር አንተ የገባኸውን ቃል እንድትፈጽም ይፈልጋል፤ ስእለትህን ካልፈጸምክ ግን ኃጢአት ይሆንብሃል።
እንግዲህ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት የምስጋና መሥዋዕት ዘወትር ለእግዚአብሔር እናቅርብ፤ ይህም ስለ ስሙ በሚመሰክሩት ከንፈሮች የሚቀርብ የምስጋና መሥዋዕት ነው።
ወደ ጌታ ኢየሱስ የምትቀርቡትም እንደ ሕያዋን ድንጋዮች መንፈሳዊ ቤት ሆናችሁ ለመታነጽ ነው፤ በዚህ ዐይነት በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ለእግዚአብሔር ለማቅረብ ቅዱሳን ካህናት ትሆናላችሁ።
እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚያስደንቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእግዚአብሔርን አስደናቂ ሥራ እንድታውጁ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ እግዚአብሔር ለራሱ ያደረጋችኹ ቅዱስ ሕዝብ ናችሁ።