Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 22:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ስለ ሠራኸው መልካም ሥራ ብዙ ሕዝብ በተሰበሰበበት ስፍራ አመሰግንሃለሁ፤ በሚፈሩህ ሰዎች ፊት ሆኜ፥ የተሳልኩትን ስለት እፈጽማለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 በታላቅ ጉባኤ የማቀርበው ምስጋናዬ ከአንተ የመጣ ነው፤ እርሱን በሚፈሩት ፊት ስእለቴን እፈጽማለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 የችግረኛን ችግር አልናቀምና፥ ቸልም አላለምና፥ ፊቱንም አልሰወረምና፥ ነገር ግን ወደ እርሱ በጮኸ ጊዜ ሰማው።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 22:25
11 Referencias Cruzadas  

በዚያን ጊዜ በሕዝብ ጉባኤ መካከል ሆኜ አመሰግንሃለሁ፤ ብዙ ሕዝብም በተሰበሰበበት ቦታ አከብርሃለሁ።


እግዚአብሔር ይመስገን! በቅኖች ሸንጎና በጉባኤም መካከል እግዚአብሔርን በሙሉ ልቤ አመሰግናለሁ።


የሚቃጠል መሥዋዕት ይዤ ወደ ቤትህ እገባለሁ፤ ስእለቴንም አቀርብልሃለሁ።


አምላክ ሆይ! እኔ ራሴ ለአንተ የስእለት ግዴታ ገብቼአለሁ፤ ስእለቴን ከምስጋና መሥዋዕት ጋር አቀርባለሁ።


የስምህን ታላቅነት ለወገኖቼ እናገራለሁ፤ እነርሱ በተሰበሰቡበት ስፍራ አመሰግንሃለሁ፤


እግዚአብሔር ያደረገልኝን ሁሉ እንድነግራችሁ፥ እግዚአብሔርን የምትፈሩ ሁሉ ኑ ስሙ።


አምላክ ሆይ! በጽዮን ሆነን አንተን ማመስገን፤ ለአንተ የተሳልነውንም መስጠት ይገባናል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios