መዝሙር 48:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሰሜን በኩል የምትገኘው፥ በከፍታዋና በውበትዋ የምትደነቀው፥ የጽዮን ተራራ የታላቁ ንጉሥ ከተማ ነች፤ እርስዋም በምድር ላሉ ሁሉ ደስታን ታጐናጽፋለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የምድር ሁሉ ደስታ የሆነው፣ በሰሜን በኩል በርቀት የሚታየው፣ በከፍታ ላይ አምሮ የደመቀው የጽዮን ተራራ፣ የታላቁ ንጉሥ ከተማ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ትልቅ ነው፥ በአምላካችን ከተማ በተቀደሰው ተራራ ምስጋናው ብዙ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሰው ልጆች ባለጠጎችና ድሆች፥ በየሀገራችሁ በአንድነት። |
አንተ እንዲህ ብለህ አስበህ ነበር፦ “ወደ ሰማይ ወጥቼ ከእግዚአብሔር ከዋክብት በላይ ዙፋኔን እዘረጋለሁ፤ በስተሰሜን ዳርቻ አማልክት በሚሰበሰቡበት ቦታ በተራራ ላይ እቀመጣለሁ።
የዘመኑ ፍጻሜ ሲደርስ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የተሠራበት ተራራ ከሌሎች ተራራዎች ሁሉ በልጦ ይታያል፤ ከኰረብቶችም ሁሉ እጅግ ከፍ ይላል፤ የብዙ መንግሥታት ሕዝቦች ወደ እርሱ ይጐርፋሉ።
የጨቋኞችሽ የልጅ ልጆች ወደ አንቺ ሲመጡ እጅ ይነሣሉ፤ የናቁሽም ሁሉ በእግርሽ ሥር ይንበረከካሉ፤ እነርሱም አንቺን “የእስራኤል ቅዱስ የእግዚአብሔር ከተማ የሆነችው ጽዮን” ብለው ይጠሩሻል።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እስራኤል ሆይ! አንቺን እንደ ልጅ አድርጌ በመቀበል፥ ከዓለም እጅግ የተዋበችውንና ለም የሆነችውን ምድር ልሰጥሽ ፈለግኹ፤ ‘አባት’ ብለሽ እንድትጠሪኝና ዳግመኛ ከእኔ እንዳትርቂ በመጠበቅ ነበር።
“ፍጹም ውብ ናት የሚሏት የዓለም መደሰቻ የነበረችው ከተማ ይህች ናትን?” እያሉ በመንገድ የሚያልፉ ሁሉ በኢየሩሳሌም ላይ እጃቸውን እያጨበጨቡ ራሳቸውን በመነቅነቅ አሽሟጠጡ።
ከግብጽ ምድር አወጣኋቸው፤ ለእነርሱ የመረጥኩላቸው ምድር በማርና በወተት የበለጸገች ነበረች፤ እርስዋም ከዓለም ምድር ሁሉ ይበልጥ የተዋበች ነበረች፤ ወደዚያች ምድርም እንደማስገባቸው ቃል የገባሁላቸው በዚያን ጊዜ ነው።
ከወደ ሰሜን የሚመጣው ወራሪ የፈለገውን ያደርጋል፤ እርሱን ቆሞ የሚመክት አይኖርም፤ እርሱ የተቀደሰችውን አገር እንኳ ሳይቀር ወሮ ይይዛታል።
በባሕሩና ቤተ መቅደሱ በተሠራበት ውብ ኮረብታ መካከል ባለው ስፍራ ታላላቅ ንጉሣዊ ድንኳኖችን ይተክላል፤ ይህም ሁሉ ሆኖ በመጨረሻው ራሱ ይጠፋል፤ የሚረዳውም አያገኝም።”
ከነዚህ ከአራቱ ቀንዶች በአንደኛው ላይ ሌላ ትንሽ ቀንድ በቀለ፤ የዚህም የትንሽ ቀንድ ኀይል ወደ ደቡብና ወደ ምሥራቅ ወደ መልካሚቱ ምድር ተስፋፋ።
እኔ ታላቅ ንጉሥ ነኝ፤ ስሜም በሕዝቦች ዘንድ የተከበረስለሆነ፥ ከበግ መንጋዎቹ መካከል አውራ በግ እያለው ለተሳለው ስለት ነውር ያለበትን በግ መሥዋዕት የሚያቀርብልኝ የተረገመ ነው!” ይላል የሠራዊት አምላክ።
እናንተ ግን ወደ ጽዮን ተራራ ቀርባችኋል፤ እርስዋ የሕያው እግዚአብሔር ከተማ የሆነችው ሰማያዊት ኢየሩሳሌም ናት፤ በደስታ ወደተሰበሰቡት፥ በብዙ ሺህ ወደሚቈጠሩት መላእክት ቀርባችኋል።