መዝሙር 45:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልቤ መልካም ርእስን ያፈልቃል፤ ጽሑፌም የሚያተኲረው በንጉሡ ላይ ነው፤ አንደበቴም እንደ መልካም ጸሐፊ ብዕር ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልቤ መልካም ሐሳብ አፈለቀ፤ የተቀኘሁትን ቅኔ ለንጉሥ አሰማለሁ፤ አንደበቴም እንደ ባለሙያ ጸሓፊ ብርዕ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለመዘምራን አለቃ፥ በመለከቶች፥ የቆሬ ልጆች ትምህርት፥ የፍቅር መዝሙር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምላካችን መጠጊያችንና ኀይላችን ነው፤ ባገኘን በታላቅ መከራም ጊዜ ረዳታችን ነው። |
ይህ ዕዝራ ከባቢሎን ወደ ኢየሩሳሌም መጣ፤ እርሱም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ለሙሴ በሰጠው ሕግ ሊቅ ነበር፤ የእግዚአብሔር ኀይል ከእርሱ ጋር ስለ ነበረ ንጉሡ የጠየቀውን ነገር ሁሉ ሰጠው።
የእስራኤል እረኛ፥ የዮሴፍን ልጆች እንደ መንጋ የምትመራ አምላክ ሆይ! በኪሩቤል ላይ ባለው ዙፋንህ ተቀምጠህ፥ ጸሎታችንን አድምጥ፤ ብርሃንህም ይብራ።
በዚያን ጊዜ ንጉሡ በቀኙ በኩል ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል፦ ‘እናንተ አባቴ የባረካችሁ! ኑ! ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ!