አሁን ግን ጣልከን፤ አዋረድከንም፤ ከሚዘምተው ሠራዊታችን ጋር አብረህ መውጣትን ትተሃል።
አሁን ግን እነሆ ትተኸናል፤ አሳፍረኸናልም፤ ከሰራዊታችንም ጋራ አትወጣም።
ሁልጊዜ በእግዚአብሔር እንከብራለን፥ ስምህንም ለዘለዓለም እናመሰግናለን።
የንግሥት ሴቶች ልጆች ለክብርህ ናቸው፤ በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች።
አምላክ ሆይ! አንተ ጥለኸናል፤ ከሠራዊታችንም ጋር ወደ ጦር ሜዳ መውጣት ትተሃል።
አንተ አምላኬ፥ ጠንካራ ምሽጌ ነህ፤ ታዲያ፥ ስለምን ትተወኛለህ? ለምንስ ጠላቶቼ እያበሳጩ ያሳዝኑኝ?
አምላክ ሆይ! እስከ አሁን ጣልከን፤ ሰባበርከን፤ እስከ አሁን ተቈጣኸን፤ አሁን መልሰን።
አምላክ ሆይ! እንደዚህ ለምን ተውከን? ሕዝብህንስ የምትቈጣው ለዘለዓለም ነውን?
እግዚአብሔር ሆይ! ለምን ትጥለኛለህ? ፊትህንስ ከእኔ ለምን ትሰውራለህ?
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ጠቢብ በጥበቡ፥ ብርቱ ሰውም በኀይሉ፥ ባለጸጋም በሀብቱ አይመካ፤
አንድ ሰው መመካት ካለበት በምድር ላይ ምሕረትን፥ ትክክለኛ ፍርድንና እውነትን የማስገኝ እኔ አምላክ መሆኔን በመረዳት ይመካ፤ እኔም ደስ የሚያሰኘኝ ይኸው ነው፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”