ጌታ ሆይ! የልቤን ፍላጎት ሁሉ ታውቃለህ፤ የእኔም መቃተት ለአንተ ምሥጢር አይደለም።
ጌታ ሆይ፤ ምኞቴ ሁሉ በፊትህ ግልጽ ነው፤ ጭንቀቴም ከአንተ የተሰወረ አይደለም።
ዛልኩኝ እጅግም ደቀቅሁ፥ ከልቤ መጠበብ የተነሣ ጮኽሁ።
ዝም አልሁ አፌንም አልከፈትሁም። አንተ ፈጥረኸኛልና፤
እግዚአብሔር ሆይ! አንተ የምስኪኖችን ጸሎት ትሰማለህ፤ ልመናቸውንም አድምጠህ ታበረታታቸዋለህ።
ይህንንም ያደረገው የእስረኞችን መቃተት ሰምቶ ሞት የተፈረደባቸውንም ነጻ ለማውጣት ነው።
ድምፄን ከፍ አድርጌ በመቃተቴ ከቈዳና ከአጥንት በቀር ሰውነት የለኝም።
ከሐዘኔ ብዛት የተነሣ ደክሜአለሁ፤ ከለቅሶዬ ብዛት የተነሣ በየሌሊቱ አልጋዬ በእንባ ይረጥባል፤ ትራሴም ይርሳል።
ናትናኤልም “የት ታውቀኛለህ?” አለው። ኢየሱስም “ፊልጶስ ሳይጠራህ በፊት ከበለስ ዛፍ ሥር ሆነህ አይቼሃለሁ” ሲል መለሰለት።
ሰማያዊ አካልን ለመልበስ በመናፈቅ እንጥራለን።