መዝሙር 38:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሆይ! በቊጣህ አትገሥጸኝ፤ በኀይለኛ ቊጣህም አትቅጣኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ በቍጣህ አትገሥጸኝ፤ በመዓትህም አትቅጣኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለሰንበት መታሰቢያ፥ የዳዊት መዝሙር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በአንደበቴ እንዳልስት አፌን እጠብቃለሁ፤ ኃጥኣን በፊቴ በተቃወሙኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ” አልሁ፤ |
እኔ ራሴ ከእናንተ ጋር በመሆን አድናችኋለሁ፤ እናንተን የበተንኩባቸውን አሕዛብ ሁሉ እደመስሳለሁ፤ እናንተን ግን አላጠፋም፤ ሆኖም ያለ ቅጣት አልተዋችሁም፤ የምቀጣችሁ ግን እንደ ጥፋታችሁ ነው፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”
እግዚአብሔር ሆይ! ስላደረግኸው አስደናቂ ሥራ ሁሉ ሰምቼ እጅግ ፈራሁ፤ አሁንም በዘመናችን የቀድሞውን ሥራህን ደግመህ አድርግ፤ በየዘመናቱም እንዲታወቅ አድርግ፤ በምትቈጣበት ጊዜ እንኳ ምሕረትህን አታርቅ።