መዝሙር 70 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉምርዳታን ለማግኘት የቀረበ ጸሎት (የመዝሙር 40፥13-17 ተመሳሳይ) 1 አምላክ ሆይ! አድነኝ! እግዚአብሔር ሆይ! ፈጥነህም እርዳኝ! 2 ሊገድሉኝ የሚፈልጉ ሁሉ ይፈሩ ግራም ይጋቡ፤ የእኔን ጒዳት የሚመኙ ሁሉ በውርደት ወደ ኋላቸው ይመለሱ። 3 እሰይ! እሰይ! እያሉ የሚያፌዙብኝ ሁሉ ዐፍረው ወደ ኋላቸው ይመለሱ። 4 አንተን የሚፈልጉ ሁሉ ደስ ይበላቸው፤ ሐሴትም ያድርጉ፤ ማዳንህን የሚወዱ ሁሉ ዘወትር “እግዚአብሔር ታላቅ ነው!” ይበሉ። 5 እኔ ጐስቋላና ምስኪን ነኝ፤ አምላክ ሆይ! ፈጥነህ ወደ እኔ ና፤ እግዚአብሔር ሆይ! ረዳቴና አዳኜ አንተ ስለ ሆንክ አትዘግይ! |