መዝሙር 35:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ይህን ተመልክተሃል፤ ስለዚህ ጌታ ሆይ! ዝም አትበል! ከእኔም አትራቅ! አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህን አይተሃልና ዝም አትበል፤ ጌታ ሆይ፤ ከእኔ አትራቅ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ፥ አንተ አየኸው፥ ዝም አትበል፥ አቤቱ፥ ከእኔ አትራቅ። |
አምላክ ሆይ! አንተ ግን ችግርንና ጭንቀትን አይተህ ልታስወግዳቸው መፍትሔ ታዘጋጃለህ፤ ችግረኛ ራሱን ለአንተ ይሰጣል፤ አንተም የሙት ልጆችን ትረዳለህ።
እግዚአብሔር ሆይ! ጸሎቴን ስማ፤ ጩኸቴንም አድምጥ፤ ሳለቅስም ቶሎ ብለህ እርዳኝ፤ እኔ ለጥቂት ጊዜ የአንተ እንግዳ ነኝ፤ እንደ ቀድሞ አባቶቼም በስደተኛነት የምኖር ነኝ።
ከዚያም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፤ “በግብጽ ያለውን የሕዝቤን ጭንቀት አይቻለሁ፤ በአስጨናቂዎቻቸው ምክንያት የሚጮኹትን ጩኸት ሰምቼአለሁ፤ ጭንቀታቸውንም ዐውቃለሁ።
በግብጽ ያለውን የሕዝቤን ጽኑ መከራ በእርግጥ አይቼአለሁ፤ የጭንቀት ጩኸታቸውንም ሰምቻለሁ፤ ስለዚህ ላድናቸው ወርጃለሁ፤ አሁንም ና! እኔ አንተን ወደ ግብጽ እልክሃለሁ።’