በዚህ ጊዜ ኢዮአብ ወደ ንጉሡ ቤት ሄዶ እንዲህ አለው፤ “የአንተን የወንዶችና የሴቶች ልጆችህን፥ የሚስቶችህንና የቊባቶችህን ሕይወት ያዳኑትን ሰዎች ዛሬ አሳፍረሃቸዋል፤
መዝሙር 34:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ እርሱ የሚመለከቱ ሁሉ ፊታቸው ይበራል፤ ፊታቸውም ከቶ በኀፍረት አይሸፈነም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ እርሱ የሚመለከቱ ያበራሉ፤ ፊታቸውም ከቶ አያፍርም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታን ፈለግሁት መለሰልኝም፥ ከምፈራውም ሁሉ አዳነኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በነፋስ ፊት እንዳለ ትቢያ ይሁኑ፥ የእግዚአብሔርም መልአክ ያስጨንቃቸው። |
በዚህ ጊዜ ኢዮአብ ወደ ንጉሡ ቤት ሄዶ እንዲህ አለው፤ “የአንተን የወንዶችና የሴቶች ልጆችህን፥ የሚስቶችህንና የቊባቶችህን ሕይወት ያዳኑትን ሰዎች ዛሬ አሳፍረሃቸዋል፤
ይህንንም አይተሽ ፈገግታሽ በደስታ ይፈካል፤ ከባሕር የሚገኘው በረከትና፥ ከሕዝቦች የሚመጣው ሀብት የአንቺ ስለሚሆን፥ ከደስታሽ ብዛት የተነሣ ልብሽ ይፈነድቃል።
የምንሮጠውም የእምነታችን መሥራችና ፈጻሚ የሆነውን ኢየሱስን በመመልከት ነው፤ እርሱ በፊቱ በተደቀነው ደስታ ምክንያት በመስቀል ላይ የመሞትን ውርደት ከምንም ሳይቈጥር የመስቀልን መከራና ሞት ታገሠ፤ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝም ተቀመጠ።
ስለዚህም ዳዊትና ስድስት መቶ የሚሆኑ ተከታዮቹ በሙሉ ወዲያውኑ ቀዒላን ለቀው ለመሄድ ተንቀሳቀሱ፤ ሳኦልም ዳዊት ከቀዒላ አምልጦ መሄዱን በሰማ ጊዜ የነበረውን ዕቅድ ተወ።