ዳዊት በኢየሩሳሌም ወደሚገኘው ቤተ መንግሥቱ በደረሰ ጊዜ፥ ቤተ መንግሥቱን እንዲጠብቁለት ትቶአቸው የነበሩትን ዐሥር ቊባቶቹን ወደ ሌላ ወስዶ በዘበኛ እንዲጠበቁ አደረገ፤ የሚያስፈልጋቸው ነገር ሁሉ እንዲሰጣቸው አዘዘ፤ ይሁን እንጂ ከእነርሱ ጋር ግንኙነት አልፈጸመም፤ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እስከ ዕለተ ሞታቸው በቤት ተወስነው እንደ መበለቶች በመሆን ኖሩ።
መዝሙር 30:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላክ ሆይ! ስላዳንከኝና ጠላቶቼ በእኔ ላይ እንዲደሰቱ ስላላደረግህ እጅግ አመሰግንሃለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ ከታች አንሥተኸኛልና፣ ጠላቶቼም በላዬ እንዳይደሰቱ አድርገሃልና፣ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለቤቱ መመረቅ ምስጋና፥ የዳዊት መዝሙር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ፥ አንተን ታመንሁ፤ ለዘለዓለምም አልፈር፤ በጽድቅህም አስጥለኝ፥ አድነኝም። |
ዳዊት በኢየሩሳሌም ወደሚገኘው ቤተ መንግሥቱ በደረሰ ጊዜ፥ ቤተ መንግሥቱን እንዲጠብቁለት ትቶአቸው የነበሩትን ዐሥር ቊባቶቹን ወደ ሌላ ወስዶ በዘበኛ እንዲጠበቁ አደረገ፤ የሚያስፈልጋቸው ነገር ሁሉ እንዲሰጣቸው አዘዘ፤ ይሁን እንጂ ከእነርሱ ጋር ግንኙነት አልፈጸመም፤ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እስከ ዕለተ ሞታቸው በቤት ተወስነው እንደ መበለቶች በመሆን ኖሩ።
ለእግዚአብሔርም መሠዊያ ሠርቶ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የአንድነት መሥዋዕት ሁሉ አቀረበ፤ እግዚአብሔርም የዳዊትን ጸሎት ሰማ፤ በእስራኤል ላይ የወረደውም የቸነፈር መቅሠፍት ከዚህ በኋላ ቆመ።
የጢሮስ ንጉሥ ኪራም ለዳዊት ቤተ መንግሥት ይሠሩለት ዘንድ አናጢዎች፥ ግንበኞችና የሊባኖስ ዛፍ እንጨት አስይዞ መልእክተኞችን ወደ ዳዊት ላከ።
ከዚያም በኋላ ዳዊት ቤተሰቡን ሰላም ለማለት ወደ ቤት ገባ፤ የሳኦል ልጅ ሜልኮል ልትቀበለው ወጣችና “የእስራኤል ንጉሥ ዛሬ ትልቅ ስም አግኝቶአል! በመኳንንቱ ገረዶች ፊት እንደ ቅሌታም ሽማግሌ እርቃኑን ገልጦአል!” አለችው።
ከዚህም በኋላ ንጉሡ ነቢዩ ናታንን “እነሆ እኔ ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት በተሠራ ቤት ውስጥ እኖራለሁ፤ የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት ግን በድንኳን ውስጥ ይኖራል!” አለው።
ሰሎሞንም ኻያ ሁለት ሺህ የቀንድ ከብቶችንና አንድ መቶ ኻያ ሺህ በጎችን የኅብረት መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ፤ በዚህም ዐይነት ንጉሥ ሰሎሞንና እስራኤላውያን ሁሉ ቤተ መቅደሱ ለእግዚአብሔር የተለየ እንዲሆን አደረጉ።
አሁን ግን በከበቡኝ ጠላቶቼ ላይ ራሴን ከፍ አደረግሁ፤ በደስታ “እልል” እያልኩ በመቅደሱ ውስጥ መሥዋዕት አቀርባለሁ፤ እየዘመርኩም እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ።
“ፍጹም ውብ ናት የሚሏት የዓለም መደሰቻ የነበረችው ከተማ ይህች ናትን?” እያሉ በመንገድ የሚያልፉ ሁሉ በኢየሩሳሌም ላይ እጃቸውን እያጨበጨቡ ራሳቸውን በመነቅነቅ አሽሟጠጡ።
“እነሆ፥ እኔ ናቡከደነፆር ለሰማይ ንጉሥ ምስጋና፥ ክብርና ውዳሴ አቀርባለሁ፤ እርሱ የሚያደርገው ነገር ሁሉ ትክክል ነው፤ መንገዱም ፍትሓዊ ነው፤ በትዕቢት የሚመሩትንም ሁሉ ማዋረድ ይችላል።”
“ከዚህ በኋላ የጦር መሪዎች ለዘማቾች እንዲህ ይበሉ፤ ‘አዲስ ቤት የሠራና አስመርቆ ያልገባበት ሰው በመካከላችሁ ይገኛልን? ይህ ከሆነ እርሱ ወደ ቤቱ ይመለስ፤ እርሱ በጦርነት ላይ ቢሞት ሌላ ሰው ቤቱን አስመርቆ ይገባበታል።