መዝሙር 3:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ማዳን የእግዚአብሔር ነው፤ እግዚአብሔር ሆይ፥ በረከትህ በሕዝብህ ላይ ይሁን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ማዳን የእግዚአብሔር ነው፤ በረከትህ በሕዝብህ ላይ ይሁን። ሴላ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተነሥ፥ አቤቱ፥ አምላኬ ሆይ፥ አድነኝ፥ አንተ የጠላቶቼን መንጋጋ መትተሃልና፥ የክፉዎችንም ጥርስ ሰብረሃልና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ማዳን የእግዚአብሔር ነው፥ በረከትህም በሕዝብህ ላይ ነው። |
የንጉሡ ስም ለዘለዓለሙ ሲታወስ ይኑር፤ ዝናውም ፀሐይ በሚወጣበት ዘመን ሁሉ ይሰማ፤ ሕዝቦች ሁሉ በእርሱ የተባረኩ ይሁኑ፤ እርሱንም “የተባረከ ነው!” ይሉታል።
በኮረብቶች ራስ ላይ ቅጥ ያጣ የባዕድ አምልኮ ፈንጠዝያ መፈጸማችን ምንም አልጠቀመንም፤ ለእስራኤል መዳን የሚገኘው ከአምላካችን ከእግዚአብሔር ብቻ ነው።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ አምላካችሁ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ የላችሁም፤ አዳኛችሁም እኔ ብቻ ነኝ።
የቃል ኪዳኑ ታቦት በተንቀሳቀሰ ጊዜ ሁሉ ሙሴ “እግዚአብሔር ሆይ! ተነሥ፤ ጠላቶችህ ይበተኑ፤ የሚጠሉህም ሁሉ ከፊትህ ይባረሩ!” ይል ነበር።
ስለዚህ እግዚአብሔር ልጁን የላከው በመጀመሪያ ለእናንተ ነበር፤ ይህንንም ያደረገው እያንዳንዳችሁን ከክፉ መንገዳችሁ በመመለስ እንዲባርካችሁ ነው።”
ስለዚህ መዳን ከእርሱ በቀር በሌላ በማንም የለም፤ እኛ ልንድንበት የሚገባን እግዚአብሔር ለሰዎች የሰጠው ስም ከእርሱ በቀር በመላው ዓለም ማንም የለም።”