ታቦቱንም አምጥተው ዳዊት ባዘጋጀለት ድንኳን ውስጥ በተመደበለት ስፍራ አኖሩት፤ ከዚህም በኋላ ዳዊት የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የአንድነት መሥዋዕት ሁሉ ለእግዚአብሔር አቀረበ።
መዝሙር 24:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ በሮች ራሳችሁን ከፍ አድርጉ፤ የክብር ንጉሥ ይገባ ዘንድ እናንተ ጥንታውያን በሮች ተከፈቱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተ ደጆች፤ ቀና በሉ፤ እናንተ የዘላለም በሮች፤ የክብር ንጉሥ እንዲገባ ብድግ በሉ! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንት በሮች ራሳችሁን ከፍ አድርጉ፥ የዘለዓለም ደጆችም ተከፈቱ፥ የክብርም ንጉሥ ይግባ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የልጅነቴን ኀጢአትና ስንፍናየን አታስብብኝ። አቤቱ፥ ስለ ቸርነትህ ብዛት፥ እንደ ምሕረትህ ዐስበኝ። |
ታቦቱንም አምጥተው ዳዊት ባዘጋጀለት ድንኳን ውስጥ በተመደበለት ስፍራ አኖሩት፤ ከዚህም በኋላ ዳዊት የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የአንድነት መሥዋዕት ሁሉ ለእግዚአብሔር አቀረበ።
ከዚህም በኋላ ካህናቱ የቃል ኪዳኑን ታቦት ተሸክመው ወደ ቤተ መቅደስ በማግባት በቅድስተ ቅዱሳኑ ውስጥ ወደ ቦታው አምጥተው በኪሩቤል ክንፍ ሥር አኖሩት።
አንቺ የጽዮን ተራራ የመንጋው መጠበቂያ ግንብ ሆይ! የተሰጠሽ ተስፋ ይፈጸማል፤ የቀድሞ ሉዐላዊነትሽ ኢየሩሳሌምም ዋና ከተማነቷ ይመለስልሻል።
አዲሱ ቤተ መቅደስ ከፊተኛው ይበልጥ የተዋበ ይሆናል፤ እኔም በዚያ ለሕዝቤ የተሟላ ሰላምን እሰጣለሁ፤” የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ይህን ተናግሮአል።
የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፥ በፊቴ መንገድን ያዘጋጅ ዘንድ መልእክተኛዬን እልካለሁ፤ የምትፈልጉት ጌታም በድንገት ወደ ቤተ መቅደሱ ይመጣል፤ በእርሱ የምትደሰቱበት የቃል ኪዳን መልእክተኛም በእርግጥ ይመጣል።”
ይልቅስ በጌታችንና በመድኀኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እርሱንም በማወቅ ከፍ ከፍ በሉ፤ ለእርሱ አሁንም ለዘለዓለምም ክብር ይሁን! አሜን።
“ጌታችንና አምላካችን ሆይ፥ ሁሉን ነገር ስለ ፈጠርክ ሁሉም ነገር የተፈጠረውና የሚኖረው (ሕይወትን ያገኘው) በአንተ ፈቃድ ስለ ሆነ ገናናነት፥ ክብርና ኀይልም ለአንተ ይገባል” ይሉ ነበር።