መዝሙር 20:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላክ ሆይ! ንጉሡን ከጠላቶቹ እጅ አድነው፤ እኛም በምንጠራህ ጊዜ ስማን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ ንጉሥን አድን፤ እኛም በጠራንህ ቀን ስማን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱ ተሰነካክለው ወደቁ፥ እኛ ግን ተነሣን፥ ጸንተንም ቆምን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፊትህ በተቈጣ ጊዜ እንደ እሳት እቶን አድርጋቸው፤ አቤቱ፥ በቍጣህ አውካቸው፥ እሳትም ትብላቸው። |
ነገር ግን የካህናት አለቆችና የሕግ መምህራን ኢየሱስ ያደረገውን ድንቅ ነገር በማየታቸውና ሕፃናትም በቤተ መቅደስ “ለዳዊት ልጅ ሆሳዕና! ምስጋና ይሁን!” እያሉ ሲጮኹ በመስማታቸው ተቈጡ።
ከሕዝቡም ፊት ለፊት ይሄዱ የነበሩትና ከኋላ ይከተሉ የነበሩት፥ “ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ ምስጋና ይሁን! በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው! ሆሳዕና! ምስጋና በአርያም ለእግዚአብሔር ይሁን!” እያሉ ይጮኹ ነበር።