ስላደረገው ድንቅ ሥራ አመስግኑት፤ ወደር ስለማይገኝለት ታላቅነቱ አመስግኑት።
ስለ ብርቱ ሥራው አመስግኑት፤ እጅግ ታላቅ ነውና አመስግኑት።
ስለ ታላላቅ ሥራዎቹ አወድሱት፥ እንደ ታላቅነቱ ብዛት አወድሱት።
በከሃሊነቱ አመስግኑት፤ እንደ ታላቅነቱ ብዛት አመስግኑት።
በዚህ ዐይነት ሰዎች ሁሉ በኀይልህ ስላደረግሃቸው ታላላቅ ሥራዎችና ስለ መንግሥትህም ታላቅ ግርማ ያውቃሉ።
እግዚአብሔር ታላቅ ነው፤ ከፍተኛ ምስጋናም የሚገባው ነው፤ ታላቅነቱም ሰው ከሚያስተውለው በላይ ነው።
በሕዝቦች መካከል ክብሩን አስታውቁ፤ ለሕዝቦችም ሁሉ ታላቅ ሥራውን አውሩ!
እግዚአብሔር ታላቅ ነው፤ ከፍ ያለ ምስጋናም ይገባዋል፤ ከአማልክትም ሁሉ ይበልጥ ሊፈራ ይገባዋል።
‘ልዑል እግዚአብሔር ሆይ! ወደ ፊት ከምታደርጋቸው ታላላቅና አስደናቂ ነገሮች ሁሉ ያሳየኸኝ የመጀመሪያውን ክፍል ብቻ እንደ ሆነ ዐውቃለሁ፤ አንተ የምታደርጋቸውን ታላላቅ ነገሮች የሚያደርግ ሌላ አምላክ በሰማይም ሆነ በምድር የለም።