እግዚአብሔርን አመስግኑ! እግዚአብሔርን በመቅደሱ አመስግኑት! የሚያስደንቅ ኀይሉ ባለበት በሰማይ አመስግኑት!
ሃሌ ሉያ። እግዚአብሔርን በመቅደሱ አመስግኑት፤ በታላቅ ጠፈሩ አመስግኑት።
ሃሌ ሉያ። ጌታን በመቅደሱ አወድሱት፥ በኃይሉ ጠፈር አወድሱት።
እግዚአብሔርን በተቀደሱ ቦታዎች አመስግኑት፤ በኀይሉ ጽናት አመስግኑት።
እግዚአብሔር በላይ ካለው ከቅዱስ ስፍራው ሆኖ ተመለከተ፤ ከሰማይ ወደ ምድር አየ።
በመቅደሱ እጆቻችሁን ለጸሎት ዘርግታችሁ እግዚአብሔርን አመስግኑ!
እግዚአብሔርን አመስግኑ! ለእግዚአብሔር አዲስ መዝሙር ዘምሩ! በምእመናን ጉባኤ አመስግኑት!
ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ፤ የሰማይ ጠፈርም፥ የእጁን ሥራ ያውጃል።
አንዱ ቀን ለሌላው ቀን ያንኑ መልእክት ያስተላልፋል፤ አንዱም ሌሊት ለሌላው ሌሊት ዕውቀቱን ያካፍላል።
የእግዚአብሔር ድምፅ አጋዘንን እንድትወልድ ያደርጋል የዛፎችን ቅጠል ያረግፋል፤ በመቅደሱም ያሉ ድምፁን ሲሰሙ “ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን!” ይላሉ።
ከኪሩቤል ራሶች በላይ ያለውን ጠፈር ተመለከትኩ፤ በኪሩቤል ላይ ከሰንፔር ዕንቊ የተሠራ ዙፋን የሚመስል ነገር አየሁ።
በዚያን ጊዜ ጠቢባን እንደ ሰማይ ብርሃን ያንጸባርቃሉ፤ ብዙ ሰዎችን በማስተማር ከክፉ መንገድ ወደ ደግ ሥራ የመለሱ ሁሉ ለዘለዓለም እንደ ሰማይ ከዋክብት ያበራሉ።”