እኔም “አምላክ ሆይ፥ ጦቢያና ሰንባላጥ ያደረጉትን ሁሉ ተመልከት፤ ፍረድባቸውም፤ ኖዓድያ የተባለችው ሴት ነቢይትና ሌሎቹም ነቢያት እኔን ለማስፈራራት ያደረጉትን ሁሉ አስብ” በማለት ጸለይኩ።
መዝሙር 137:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሆይ! ኢየሩሳሌም በተያዘችበት ቀን ኤዶማውያን ያደረጉትን አስብ፤ “እስከ መሠረትዋ አፈራርሳችሁ ጣሉአት!” እያሉ መጮኻቸውንም አስታውስ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ ኢየሩሳሌም በወደቀችበት ቀን፣ ኤዶማውያን እንዴት እንደ ዛቱ ዐስብ፤ ደግሞም፣ “አፍርሷት፤ ፈጽማችሁ አፈራርሷት!” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ፥ በኢየሩሳሌም ቀን የኤዶምን ልጆች አስብ፦ እስከ መሠረትዋ ድረስ አፍርሱ አፍርሱ ያሉአትን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመከራ መካከል እንኳ ብሄድ፥ አንተ ታድነኛለህ፤ በጠላቶች ቍጣ ላይ እጆችህን ትዘረጋለህ፥ ቀኝህም ያድነኛል |
እኔም “አምላክ ሆይ፥ ጦቢያና ሰንባላጥ ያደረጉትን ሁሉ ተመልከት፤ ፍረድባቸውም፤ ኖዓድያ የተባለችው ሴት ነቢይትና ሌሎቹም ነቢያት እኔን ለማስፈራራት ያደረጉትን ሁሉ አስብ” በማለት ጸለይኩ።
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን “ዘወትር ሲታወስ እንዲኖር የዚህን ድል ታሪክ ጻፈው፤ ለኢያሱም ዐማሌቃውያንን ከምድር ጨርሼ የማጠፋቸው መሆኔን ንገረው” አለው።
የእስራኤል ምድር ባድማ በመሆኑ እንደ ተደሰታችሁ እኔም የሴኢርን ተራራና የኤዶምን ግዛት ሁሉ ባድማ አደርጋለሁ፤ ከዚያ በኋላ ሁሉም እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ያውቃል።”
ነገር ግን እኔ ይህን ሁሉ ክፋታቸውን እንደማስታውስ ከቶ አይገነዘቡም፤ ከዚህ የተነሣ በገዛ ኃጢአታቸው ተከበዋል፤ ክፉ ሥራቸው ሁሉ ከእኔ የተሰወረ አይደለም።”
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የኤዶም ሕዝብ ደጋግመው ስለ ሠሩት ኃጢአት ያለ ጥርጥር እቀጣቸዋለሁ፤ እነርሱ ወንድሞቻቸውን እስራኤላውያንን በሰይፍ አሳደዋቸዋል፤ ከያዙአቸውም በኋላ ርኅራኄ አላደረጉላቸውም፤ በእነርሱ ላይ ያላቸው ቊጣ ሊበርድም አልቻለም፤
ሕዝብህን ለመታደግ፥ ቀብተህ ያነገሥከውንም ንጉሥ ለማዳን ወጣህ፤ የጥፋት አገር መሪ የሆነውን ቀጠቀጥከው፤ ተከታዮቹንም አጥፍተህ እርቃኑን አስቀረኸው። ከእግር እስከ ራሱም አራቈትከው።
እስራኤላውያን ከግብጽ በወጡ ጊዜ አማሌቃውያን በመንገድ ላይ እየተቃወሙ አስቸግረዋቸው ስለ ነበረ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር አማሌቃውያንን ለመቅጣት ወስኖአል።