እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፥ አሁን ተነሥተህ ከኀያሉ ታቦትህ ጋር ወደ ማረፊያ ቦታህ ና፤ እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፥ ካህናትህ ደኅንነትን ይልበሱ፤ ታማኞችህም በበረከትህ ይደሰቱ፤
መዝሙር 132:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ካህናትህ የጽድቅን ሥራ ይሥሩ! ታማኞችህ በደስታ ይዘምሩ! አዲሱ መደበኛ ትርጒም ካህናትህ ጽድቅን ይልበሱ፤ ቅዱሳንህም እልል ይበሉ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ካህናትህ ጽድቅን ይልበሱ፥ ጻድቃንህም ደስ ይበላቸው። |
እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፥ አሁን ተነሥተህ ከኀያሉ ታቦትህ ጋር ወደ ማረፊያ ቦታህ ና፤ እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፥ ካህናትህ ደኅንነትን ይልበሱ፤ ታማኞችህም በበረከትህ ይደሰቱ፤
እኔ በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል፤ ሁለንተናዬም በአምላኬ ሐሴትን ያደርጋል፤ የአበባ አክሊል በራሱ ላይ እንደሚያደርግ ሙሽራ፥ በጌጣጌጥም እንዳሸበረቀች ሙሽሪት አድርጎ፥ የመዳንን ልብስ አልብሶኛል፤ የጽድቅንም መጐናጸፊያ ደርቦልኛል።
አገልጋዮቼ ከልባቸው ደስታ የተነሣ ይዘምራሉ፤ እናንተ ግን ከልብ ሐዘን የተነሣ ታላቅሳላችሁ፤ ከመንፈስም ጭንቀት የተነሣ ዋይ፥ ዋይ ትላላችሁ።
የጽዮን ልጅ ሆይ! ዘምሪ! የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! ዘምሩ! እልልም በሉ! የኢየሩሳሌምም ሕዝብ ሆይ! በሙሉ ልባችሁ ደስ ይበላችሁ! ሐሴትም አድርጉ።
ጽዮን ሆይ! ደስ ይበልሽ! ኢየሩሳሌም ሆይ! በደስታ እልል በይ! እነሆ ንጉሥሽ ትሑት ሆኖ፥ በአህያይቱ ማለትም በውርንጫይቱ ላይ ተቀምጦ፥ በድል አድራጊነት ወደ አንቺ ይመጣል።
እንዲሁም እናንተ ጐልማሶች! ለሽማግሌዎች ታዘዙ፤ ሁላችሁም ትሕትናን እንደ ልብስ ለብሳችሁ አንዱ ሌላውን ያገልግል፤ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል ለትሑቶች ግን ጸጋን ይሰጣል” ተብሎ ተጽፎአልና።
እግዚአብሔር ሆይ! ጠላቶችህን ሁሉ በዚህ ዐይነት አጥፋ፤ ወዳጆችህ ግን እንደ ንጋት ፀሐይ ይድመቁ። ከዚህ በኋላ በምድሪቱ ላይ አርባ ዓመት ሙሉ ሰላም ሆነ።