9 ካህናትህ ጽድቅን ይልበሱ፥ ጻድቃንህም ደስ ይበላቸው።
9 ካህናትህ ጽድቅን ይልበሱ፤ ቅዱሳንህም እልል ይበሉ።”
9 ካህናትህ የጽድቅን ሥራ ይሥሩ! ታማኞችህ በደስታ ይዘምሩ!
አሁንም፥ አቤቱ አምላክ ሆይ! ተነሥተህ አንተና የኃይልህ ታቦት ወደ ማረፍያ ስፍራህ ሂዱ፤ አቤቱ አምላክ ሆይ! ካህናትህ ደኅንነትን ይልበሱ፤ ቅዱሳንህም በደስታ ደስ ይበላቸው።
ጽድቅን ለበስሁ እርሷም ለበሰችኝ፥ ፍርዴም እንደ ካባና እንደ ቆብ ነበረ።
ነፍሴ ሆይ፥ ጌታን ባርኪ፥ አቤቱ አምላኬ ሆይ፥ አንተ እጅግ ታላቅ ነህ፥ ክብርንና ግርማን ለበስህ።
ካህናትዋንም ደኅንነትን አለብሳቸዋለሁ፥ ጻድቃኗም እጅግ ደስ ይላቸዋል።
ቅዱሳን በክብር ይመካሉ፥ በምንጣፋቸውም ላይ ሐሤትን ያደርጋሉ።
ለመዘምራን አለቃ፥ የቆሬ ልጆች መዝሙር።
ጢስ እንደሚበንን እንዲሁ ይብነኑ፥ ሰም በእሳት ፊት እንደሚቀልጥ፥ እንዲሁ ክፉዎች ከእግዚአብሔር ፊት ይጥፉ።
እሰይ እሰይ የሚሉኝ አፍረው ወዲያው ወደ ኋላቸው ይመለሱ።
ጌታ ነገሠ፥ ግርማን ተጐናጸፈ፥ ጌታ ኃይልን ለበሰ፥ ታጠቀም፥ ዓለምን እንዳትናወጥ አጸናት።
አክሊልን እንደ ለበሰ ሙሽራ፥ በጌጥ ሽልማትዋም እንዳጌጠች ሙሽራ፥ የማዳንን ልብስ አልብሶኛልና፥ የጽድቅንም መጐናጸፊያ ደርቦልኛልና በጌታ እጅግ ደስ ይለኛል፥ ነፍሴም በአምላኬ ሐሤት ታደርጋለች።
እነሆ፥ አገልጋዮቼ ከልባቸው ደስታ የተነሣ ይዘምራሉ፥ እናንተ ግን ከልባችሁ ኀዘን የተነሣ ትጮኻላችሁ፥ መንፈሳችሁም ስለ ተሰበረ ወዮ ትላላችሁ።
የጽዮን ልጅ ሆይ፥ ዘምሪ፤ እስራኤል ሆይ፥ እልል በሉ፤ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ በፍጹም ልብሽ ሐሴት አድርጊ ደስም ይበልሽ።
አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እጅግ ደስ ይበልሽ! አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ እልል በዪ! እነሆ፥ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፤ ትሑትም ሆኖ በአህያም፥ በአህያይቱ ግልገል በውርጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል።
ነገር ግን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ልበሱት፤ የሥጋም ሐሳብ ምኞቱን እንዲፈጽም አትፍቀዱለት።
እንዲሁም እናንተ ጐልማሶች! ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም ትሕትናን እንደ ልብስ ለብሳችሁ አንዱ ሌላውን ያገልግል፤ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታኑ ግን ጸጋን ይሰጣል” ተብሎ ተጽፎአልና።
ያጌጠና የተጣራ ቀጭን የተልባ እግር ልብስ እንድትለብስ ተሰጥቶአታል።” ቀጭኑ የተልባ እግር የቅዱሳን የጽድቅ ሥራ ነውና።
አቤቱ፥ ጠላቶችህ ሁሉ እንዲሁ ይጥፉ፥ ወዳጆችህ ግን ፀሐይ በኃይሉ በወጣ ጊዜ እንደሚሆን፥ እንዲሁ ይሁኑ። ምድሪቱም አርባ ዓመት ያህል ዐረፈች።