10 ስለ አገልጋይህ ስለ ዳዊት ስትል መርጠህ የቀባኸውን አትተወው።
10 ስለ ባሪያህ ስለ ዳዊት ስትል፣ የቀባኸውን ሰው አትተወው።
10 ስለ ዳዊት ስለ ባርያህ ብለኽ የቀባኸውን ሰው ፊት አትመልስ።
ከዚህ ጊዜ በኋላ እስራኤላውያን ወደ አምላካቸው ወደ እግዚአብሔርና ወደ ንጉሣቸው ወደ ዳዊት ይመለሳሉ፥ በኋለኛው ዘመን በፍርሃት ወደ እግዚአብሔር ይመጣሉ፤ በረከቱንም ይቀበላሉ።
አምላክ ሆይ! መርጠህ የቀባኸውን ንጉሣችንን ባርከው፤ ጋሻችን ስለ ሆነም ተመልከተው።
እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፥ የቀባኸውን ንጉሥ አትተወው፤ ለአገልጋይህ ለዳዊት ያደረግህለትን ፍቅር አስታውስ።”
ስለ ራሴ ክብር እንዲሁም ለአገልጋዬ ለዳዊት ስለ ሰጠሁት የተስፋ ቃል ይህችን ከተማ እኔ ራሴ ተከላክዬ አድናታለሁ።”
ይሁን እንጂ ከሰሎሞን መንግሥትን በሙሉ አልወስድበትም፤ በሕይወት እስካለም ድረስ በሥልጣን እንዲቈይ አደርገዋለሁ፤ ይህንንም የማደርገው ለመረጥኩትና ሕጎቼንና ትእዛዞቼን ለፈጸመው ለአገልጋዬ ለዳዊት ስል ነው።
እግዚአብሔር ግን ከዘሩ መንግሥትን እንደማያጠፋ ለአገልጋዩ ለዳዊት ተስፋ ሰጥቶት ስለ ነበር ይሁዳን መደምሰስ አልፈለገም።
በሌላ ስፍራ አንድ ሺህ ቀን ከመቈየት በመቅደስህ አንድ ቀን መዋል የተሻለ ነው፤ በክፉዎች ቤት ከምኖር ይልቅ በእግዚአብሔር ቤት ዘበኛ ሆኜ መኖርን እመርጣለሁ።
አንተ ለነገሥታት ድልን ታጐናጽፋለህ፤ አገልጋይህን ዳዊትንም ከስለታም ሰይፍ ትታደገዋለህ።