መዝሙር 132:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሆይ! ለአንተ የገባውን ቃል ኪዳንና ሁሉን ለምትችል ለያዕቆብ አምላክ ለአንተ እንዲህ ሲል የተሳለውን ስእለት አስታውስ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱ ለእግዚአብሔር ማለ፤ ለያዕቆብም ኀያል አምላክ እንዲህ ሲል ተሳለ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለጌታ እንደማለ፥ ለያዕቆብም ኀያል እንደ ተሳለ፦ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከራሱ ጀምሮ እስከ ጢሙ፥ በልብሱ መደረቢያ ላይ፥ እስከሚወርደው እስከ አሮን ጢም ድረስ እንደሚፈስ ሽቱ ነው። |
ከዚህም በኋላ ንጉሡ ነቢዩ ናታንን “እነሆ እኔ ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት በተሠራ ቤት ውስጥ እኖራለሁ፤ የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት ግን በድንኳን ውስጥ ይኖራል!” አለው።
ሁሉም በተሰበሰቡ ጊዜ ዳዊት ተነሥቶ፥ እንዲህ አለ፦ “ወገኖቼ ሆይ፥ አድምጡኝ፤ ለአምላካችን የእግር ማሳረፊያ ይሆን ዘንድ የተቀደሰው ታቦት የሚያርፍበት ቤት ለመሥራት ፈልጌ ነበር፤ ለቤተ መቅደሱም ሕንጻ ማሠሪያ የሚሆነውን ዕቃ ሁሉ አዘጋጅቼአለሁ፤
ጨቋኞችሽ የገዛ ሥጋቸውን እንዲበሉ አደርጋለሁ፤ በወይን ጠጅ እንደሚሰክሩ የገዛ ደማቸውን ጠጥተው እንዲሰክሩ አደርጋለሁ። ከዚህም የተነሣ እኔ እግዚአብሔር አዳኝሽና ታዳጊሽ የእስራኤል ኀያል አምላክ መሆኔን የዓለም ሕዝብ ሁሉ ያውቃል።”
ልጆች የእናታቸውን ጡት እንደሚጠቡ የአንቺም ልጆች የሕዝቦችንና የነገሥታትን ሀብት በመውሰድ ይጠቀሙበታል፤ አንቺም እኔ እግዚአብሔር አዳኝሽና ታዳጊሽ ኀያሉ የያዕቆብ አምላክ መሆኔን ታውቂአለሽ።