106 እውነተኛ ትእዛዞችህን ለመጠበቅ በመሐላ የገባሁትን ቃል አጸናለሁ።
106 የጽድቅ ሕግህን ለመጠበቅ፤ ምያለሁ፤ ይህንኑ አጸናለሁ።
106 የጽድቅህን ፍርድ እጠብቅ ዘንድ ማልሁ፥ አጸናሁም።
እነዚህ ሁሉ ወንድሞቻቸው ከሆኑት መሪዎቻቸው ጋር ተባብረው በእግዚአብሔር አገልጋይ በሙሴ አማካይነት ለተሰጡት ለጌታችን ለእግዚአብሔር ትእዛዞች፥ ሥርዓቶችና ድንጋጌዎች ሁሉ ታዛዦች እንደሚሆኑ በእርግማንና በመሐላ ቃል ገቡ።
አምላክ ሆይ! እኔ ራሴ ለአንተ የስእለት ግዴታ ገብቼአለሁ፤ ስእለቴን ከምስጋና መሥዋዕት ጋር አቀርባለሁ።
እነርሱ ያደረጉት እኛ ከጠበቅነው በላይ ነው፤ በመጀመሪያ ራሳቸውን ለጌታ ሰጡ፤ ቀጥሎም በእግዚአብሔር ፈቃድ ራሳቸውን ለእኛ ሰጥተዋል።
ንጉሡ በዐምዱ አጠገብ ቆሞ በሙሉ ልቡና ሓሳቡ እግዚአብሔርን ለመከተልና ትእዛዞቹን፥ ደንቦቹንና ድንጋጌዎቹን ለመጠበቅ በእርሱ ፊት ቃል ኪዳኑን አደሰ፤ ስለዚህም በዚህ መጽሐፍ የተጻፈውን ቃል ኪዳን አረጋገጠ፤ ሕዝቡም በቃል ኪዳኑ ተባበረ።
እናንተ ክፉ አድራጊዎች ከእኔ ወዲያ ራቁ፤ እኔ የአምላኬን ትእዛዞች መጠበቅ እፈልጋለሁ።
ደግሞም ለቀደሙ ሰዎች “በሐሰት አትማሉ፤ ነገር ግን መሐላችሁን ለጌታ ፈጽሙ” የተባለውን ሰምታችኋል።
ሕዝቡም እንዲህ ሲሉ መለሱለት፤ “እግዚአብሔርን ትተን ሌሎች ባዕዳን አማልክትን ማምለክ ከእኛ ይራቅ!
ንጉሡ በዐምዱ አጠገብ ቆሞ በሙሉ ልቡና ሐሳቡ እግዚአብሔርን ለመከተልና ትእዛዞቹን፥ ደንቦቹንና ድንጋጌዎቹን ለመጠበቅ በእርሱ ፊት ቃል ኪዳኑን አደሰ፤ ስለዚህም በዚህ መጽሐፍ የተጻፈውን ቃል ኪዳን አረጋገጠ።
በአካባቢአችን ላሉት አሕዛብ ሴቶች ልጆቻችንን በጋብቻ እንደማንሰጥና ወይም የእነርሱን ሴቶች ልጆች ለወንዶች ልጆቻችን በጋብቻ እንደማንወስድ ቃል እንገባለን።