መዝሙር 12:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእግዚአብሔር የተስፋ ቃሎች የታመኑ ናቸው፤ በእሳት ምድጃ ሰባት ጊዜ እንደ ነጠረ ብር የጠሩ ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔር ቃል የጠራ ቃል ነው፤ ሰባት ጊዜ እንደ ተጣራ፣ በምድር ላይ በከውር እንደ ተፈተነ ብር ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለ ምስኪኖች መከራ፥ ስለ ችግረኞች ጩኸት ጌታ፦ አሁን እነሣለሁ ይላል፥ የተጠሙትንም ደኅንነት አመጣላቸዋለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የረዳኝን እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ፤ ለልዑል እግዚአብሔር ስምም እዘምራለሁ። |
ከዚያም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፤ “በግብጽ ያለውን የሕዝቤን ጭንቀት አይቻለሁ፤ በአስጨናቂዎቻቸው ምክንያት የሚጮኹትን ጩኸት ሰምቼአለሁ፤ ጭንቀታቸውንም ዐውቃለሁ።
እነርሱንም ከግብጻውያን እጅ ለማዳን ወርጃለሁ፤ ከግብጽም አውጥቼ አሁን ከነዓናውያን፥ ሒታውያን፥ አሞራውያን፥ ፈሪዛውያን፥ ሒዋውያንና ኢያቡሳውያን፥ የሚኖሩባትን፥ በማርና በወተት የበለጸገችውን ሰፊና ለም የሆነችውን ምድር እሰጣቸዋለሁ።
እግዚአብሔርም ሙሴን “በንጉሡ በፈርዖን ላይ የማደርገውን አሁን ታያለህ፤ በኀይሌ ተገዶ ሕዝቤን ይለቃል፤ በኀያል ክንዴም ተሸንፎ ያባርራቸዋል።”
የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል “በባቢሎን ላይ አደጋ ጥዬ አፈራርሳታለሁ፤ ምንም ነገር አላስቀርላትም፤ ለዘር እንኳ የሚተርፍ ትውልድ አይኖራትም፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።