Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ምሳሌ 30:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 “እግዚአብሔር የሚናገረው ቃል ሁሉ እውነት ነው፤ ለሚታመኑበት ሁሉ ጋሻ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 “የእግዚአብሔር ቃል የነጠረ ነው፤ እርሱ ለሚታመኑበት ሁሉ ጋሻቸው ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 የእግዚአብሔር ቃል ሁሉ የጠራ ነው፥ እርሱ ለሚታመኑት ጋሻ ነው።

Ver Capítulo Copiar




ምሳሌ 30:5
17 Referencias Cruzadas  

የአምላክ መንገድ ፍጹም ነው! ቃሉም ተጠራ ነው! እርሱን መጠጊያ ለሚያደርጉት ሁሉ ጋሻቸው ነው።


ነገር ግን ከእግዚአብሔር የሚገኘው ጥበብ በመጀመሪያ ንጹሕ ነው፤ ቀጥሎም ሰላም ወዳድ፥ ደግ፥ ታዛዥ፥ ምሕረት አድራጊ፥ ጥሩ ፍሬ የሞላበት፥ አድልዎና ግብዝነት የሌለበት ነው።


ጌታችንና አምላካችን ሆይ! አንተ እንደ ፀሐይና እንደ ጋሻ ነህ፤ በቸርነትና በክብር ትጠብቀናለህ፤ ደግ ለሚሠሩ ሰዎች ማናቸውንም መልካም ነገር አትከለክላቸውም።


የእግዚአብሔር የተስፋ ቃሎች የታመኑ ናቸው፤ በእሳት ምድጃ ሰባት ጊዜ እንደ ነጠረ ብር የጠሩ ናቸው።


እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ግን ጋሻዬ ነህ፤ ድልን በማጐናጸፍ ክብርን የምትሰጠኝ አንተ ነህ።


የተስፋ ቃልህ እጅግ የታመነ ነው፤ እኔም በጣም እወደዋለሁ።


እግዚአብሔርን “አንተ መከታዬና መጠጊያዬ ነህ፤ አንተ የምተማመንብህ አምላኬ ነህ” ይለዋል።


ከዚህ በኋላ አብራም ራእይ አየ፤ እግዚአብሔርም “አብራም፥ አትፍራ፤ እንደ ጋሻ ሆኜ ከአደጋ ሁሉ እጠብቅሃለሁ፤ ታላቅ በረከትም እሰጥሃለሁ” ሲል ሰማው።


ስለዚህ ሕግ ቅዱስ ነው፤ ትእዛዝም ቅዱስና እውነት መልካምም ነው።


እግዚአብሔር ጠባቂዬና መከታዬ ነው፤ መጠለያዬና አዳኜ ነው፤ በእርሱ ተማምኜ በሰላም እኖራለሁ፤ እርሱ አሕዛብን ከእግሬ በታች አድርጎ ያስገዛልኛል።


የእግዚአብሔር ሕግ ትክክል ነው፤ ለልብ ደስታን ይሰጣል፤ የእግዚአብሔር ትእዛዝ ብሩህ ነው፤ ለዐይን ብርሃንን ይሰጣል።


የእግዚአብሔር መንገድ ፍጹም ነው፤ ቃሉ የጠራ ነው፤ እርሱን መጠጊያ ለሚያደርጉት ሁሉ ጋሻቸው ነው።


እግዚአብሔር አለቴ፥ አምባዬና አዳኜ ነው፤ አምላኬ የምጠጋበት አለቴ ነው፤ እርሱ ጋሻዬና የመዳኔ ቀን፥ ጠንካራ መመኪያም ነው።


እርሱ ለቀጥተኞች መልካም ጥበብን ይሰጣል፤ በተግባራቸው ነቀፋ ለሌለባቸው ጋሻቸው ነው።


ከእግዚአብሔር በቀር ማነው አምላክ? ከእርሱስ በቀር መጠጊያ የሚሆን ማነው?


ሰውን የሚፈራ ችግር ላይ ይወድቃል፤ በእግዚአብሔር የሚታመን ግን በሰላም ይኖራል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios