La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መዝሙር 118:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ሆኖ ስለሚረዳኝ፥ የጠላቶቼን ውድቀት አያለሁ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ይረዳኝ ዘንድ እግዚአብሔር ከእኔ ጋራ ነው፤ የጠላቶቼንም ውድቀት አያለሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጌታ ሊረዳኝ ከጎኔ ነው፥ እኔም ጠላቶቼን በኩራት አያለሁ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አቤቱ፥ የጽ​ድ​ቅ​ህን ፍርድ ስማር በቅን ልብ አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ።

Ver Capítulo



መዝሙር 118:7
10 Referencias Cruzadas  

የእግዚአብሔር መንፈስ የሠላሳዎቹ መሪ በሆነው በዐማሳይ ላይ ወረደ፤ እርሱም፦ “ዳዊት ሆይ! እኛ የአንተ ነን! የእሴይ ልጅ ዳዊት ሆይ! እኛ ከአንተ ጋር ነን! ለአንተና አንተን ለሚረዱ ሁሉ ሰላም ይሁን! እግዚአብሔር ከአንተ ጋር በመሆን ይረዳሃል፤” በማለት ድምፁን ከፍ አድርጎ ጮኸ፤ ዳዊትም እነርሱን በደስታ ተቀብሎ በሠራዊቱ ውስጥ አለቆች አደረጋቸው።


በእግዚአብሔር ያለው እምነት እጅግ የጸና ስለ ሆነ ከቶ አይፈራም፤ በመጨረሻም የጠላቶቹን ውድቀት ያያል።


ነገር ግን አምላክ ረዳቴ ነው፤ ጌታም የሕይወቴ ደጋፊ ነው።


መሥዋዕትህን በፍላጎቴ አቀርብልሃለሁ፤ እግዚአብሔር ሆይ፥ ተገቢ ስለ ሆነ ለስምህ ምስጋና አቀርባለሁ


ከችግሬ ሁሉ አድነኸኛል፤ የጠላቶቼንም ውድቀት አየሁ።


እጅግ ከበዙ ጠላቶቼ ጋር ከማደርገው ጦርነት በሰላም ይመልሰኛል።


አምላኬ በዘለዓለማዊ ፍቅሩ በፊቴ ይሄዳል፤ ጌታዬ፥ ጠላቶቼን በንቀት ዐይን እንድመለከታቸው ያደርገኛል።


መከታችን እግዚአብሔር ሆይ! ወገኖቼ የአንተን ተበቃይነት እንዳይረሱ፥ አትግደላቸው፤ ነገር ግን በኀይልህ በትናቸው፤ አዋርዳቸውም።


የጠላቶቼን መሸነፍ አየሁ፤ የአስጨናቂዎቼንም ውድቀት ሰማሁ።


‘አይዞህ አትፍራ፥ አትደንግጥ፥ ቀኝ እጅህን ይዤ እረዳሃለሁ’ እያልኩ የማበረታታህ፥ እኔ አምላክህ እግዚአብሔር ነኝ።”