መዝሙር 118:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በጻድቃን ድንኳን ውስጥ እንዲህ የሚል የድል አድራጊነት ድምፅ ይሰማል፦ “የእግዚአብሔር ኀይል ያሸንፋል!” አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጻድቃን ድንኳን የእልልታና የሆታ ድምፅ፣ እንዲህ እያለ ያስተጋባል፤ “የእግዚአብሔር ቀኝ እጅ ብርቱ ሥራ ሠራች፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእልልታና የመዳን ድምፅ በጻድቃን ድንኳን ነው፥ የጌታ ቀኝ እጅ ኃይሉን አከናወነ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ትእዛዝህን አሰላሰልሁ፥ መንገድህንም እፈልጋለሁ። |
እነርሱ ምድርን የወረሱት በሰይፋቸው አይደለም፤ ድል አድርገው የወሰዱትም በራሳቸው ኀይል አይደለም፤ ይህን ሁሉ ያደረጉት አንተ ስለ ወደድካቸውና ከእነርሱም ጋር በመሆን በኀይልህና በብርታትህ ስለ ረዳሃቸው ነው።
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “አገልጋዮቼ ይበላሉ፤ እናንተ ግን ትራባላችሁ፤ አገልጋዮቼ ይጠጣሉ እናንተ ግን ትጠማላችሁ፤ አገልጋዮቼ ይደሰታሉ፤ እናንተ ግን ኀፍረት ይደርስባችኋል።
እናንተ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆቻችሁ፥ ከወንዶችና ከሴቶች አገልጋዮቻችሁ፥ እንዲሁም ከእናንተ ጋር የርስት ክፍያ ከሌላቸው በከተሞቻችሁ ከሚኖሩ ከሌዋውያን ጋር በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት ትደሰታላችሁ።
ሰማይ ሆይ! በእርስዋ ደስ ይበልህ! እግዚአብሔር ስለ እናንተ በእርስዋ ላይ ስለ ፈረደባት እናንተ ቅዱሳንና ሐዋርያት ነቢያትም ደስ ይበላችሁ!