በምድሪቱ ላይ የሚኖሩትን ሰዎች ሁሉ ከፊታችሁ አስወጡአቸው፤ ከድንጋይና ከብረት የተሠሩትን ጣዖቶቻቸውንም ሰባበሩ፤ በኮረብታ ላይ ያሉ መስገጃዎቻቸውንም አፈራርሱ።
መዝሙር 106:34 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ባዘዛቸው መሠረት አሕዛብን አላጠፉም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ባዘዛቸው መሠረት፣ ሕዝቦችን ከማጥፋት ወደ ኋላ አሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ እንዳላቸው አሕዛብን አላጠፉም፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በተቀመጡባት ሰዎች ክፋት ፍሬያማዋን ምድር ጨው አደረጋት። |
በምድሪቱ ላይ የሚኖሩትን ሰዎች ሁሉ ከፊታችሁ አስወጡአቸው፤ ከድንጋይና ከብረት የተሠሩትን ጣዖቶቻቸውንም ሰባበሩ፤ በኮረብታ ላይ ያሉ መስገጃዎቻቸውንም አፈራርሱ።
እግዚአብሔር አምላክህ እነዚህን ሁሉ ሕዝቦች ለእናንተ አሳልፎ ሲሰጣቸውና እነርሱን ድል በምትነሣበት ጊዜ ሁሉንም መደምሰስ አለብህ፤ ከእነርሱ ጋር ምንም ዐይነት ውል አታድርግ፤ አትራራላቸውም።
ነገር ግን የይሁዳ ሕዝብ በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን ኢያቡሳውያንን ማባረር አልቻሉም፤ ስለዚህም ኢያቡሳውያን እስከ አሁን ድረስ በኢየሩሳሌም ከይሁዳ ሕዝብ ጋር ይኖራሉ።
እነዚህ ኤፍሬማውያን ግን በጌዜር የሚኖሩ ከነዓናውያንን አላስወጡም ነበር፤ ስለዚህም ከነዓናውያን እስከ አሁን ድረስ በኤፍሬማውያን መካከል ይኖራሉ፤ ሆኖም ለኤፍሬማውያን የጒልበት ሥራ ለመሥራት ይገደዳሉ።
እግዚአብሔር ከይሁዳ ሕዝብ ጋር ስለ ነበረ የተራራማውን አገር አሸንፈው ያዙ፤ ነገር ግን በረባዳማው ሜዳ አገር የነበሩት ኗሪዎች የብረት ሠረገሎች ስለ ነበሩአቸው ሊያስወጡአቸው አልቻሉም።
የብንያም ነገድ ግን በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን ኢያቡሳውያንን አላስወጡም ነበር፤ ከዚያን ጊዜም ጀምሮ ኢያቡሳውያን ከብንያም ሕዝብ ጋር እስከ ዛሬ ድረስ አብረው መኖርን ቀጠሉ።
እናንተ በዚች ምድር ከሚኖሩ ሕዝብ ጋር ምንም ዐይነት ቃል ኪዳን አታድርጉ፤ መሠዊያዎቻቸውንም አፍርሱ፤’ እናንተ ግን አልታዘዛችሁኝም፤ ይህንስ ያደረጋችኹት ለምንድን ነው?
ሄደህ በዐማሌቃውያን ላይ አደጋ በመጣል ያላቸውን ሁሉ ደምስስ፤ ከእነርሱ ምንም ነገር አታስቀር፤ ወንዶችን፥ ሴቶችን፥ ልጆችንና ሕፃናትን፥ ከብቶችን፥ በጎችን፥ ግመሎችንና አህዮችን ሁሉ ግደል።”