እግዚአብሔር በሚሠራው ሁሉ ጻድቅ ነው፤ ለተጨቈኑት ፍትሕን ይሰጣል።
እግዚአብሔር ለተጨቈኑ ሁሉ፣ ቅን ፍርድንና ፍትሕን ይሰጣቸዋል።
ጌታ ጽድቅን ይፈጽማል፥ ለተበደሉ ሁሉ ይፈርዳል።
ጥልቁም እንደ ልብስ ክዳኗ ነው፥ በተራሮችም ላይ ውኆች ይቆማሉ።
ምክንያቱም እርሱ ሊገድሉት ከተዘጋጁ ሰዎች እጅ ሊያድነው ስለ ድኻ ሰው መብት ይከራከራል፤
እግዚአብሔር ግን “ችግረኞች ተጨቊነዋል፤ ስደተኞች በመከራ ብዛት ይቃትታሉ፤ ስለዚህ እነርሱ የሚፈልጉትን ደኅንነት ለመስጠት እነሣለሁ” ይላል።
ለተጨቈኑት ፍትሕን ይሰጣል፤ ለተራቡ ምግብን ይሰጣል። እስረኞችን ነጻ ያወጣል።
ጌታ ሆይ! ሁለመናዬ እንዲህ ብሎ ይናገራል፤ ተበዳዮችን ከበደለኛ የሚያድን፥ ድኾችንና ተጨቋኞችን ከነጣቂዎች የሚጠብቅ እንደ አንተ ያለ ማነው?
ወደ እርሱ የሚጮኹትን ድኾች፥ ችግረኞችንና የተጨቈኑትን ሰዎች ነጻ ያወጣል።
በሕዝቡ መካከል ለተጨቈኑት ፍርድን ይስጥ፤ ችግረኞችንም ይርዳ፤ ጨቋኝንም ይደምስስ
እግዚአብሔር ለተጨቈኑት መጠጊያ ነው፤ በመከራ ጊዜም መከላከያ አምባ ነው።
ድኾችን ማስጨነቅ ፈጣሪን መናቅ ነው፤ ለድኾች ቸርነትን ማድረግ ግን እግዚአብሔርን እንደ ማክበር ይቈጠራል።
የቈየውን የወሰን ምልክት አትለውጥ፤ እንዲሁም አባትና እናት የሌላቸውን ልጆች መሬት አትቀማ፤
በውስጥሽም አባትና እናት ይናቃሉ፤ የውጪ አገር ሰዎች ይታለላሉ፤ ባሎቻቸው የሞቱባቸው ሴቶችና አባትና እናት የሌላቸው ልጆች ይበደላሉ።
አገልጋዩም ተመልሶ መጣና ጌታውን ‘ጌታዬ ሆይ! እነሆ፥ ያዘዝከኝን ሁሉ ፈጽሜአለሁ፤ ሆኖም ገና ትርፍ ቦታ አለ’ አለው።
እናንተ ግን ድኾችን ትንቃላችሁ፤ የሚጨቊኑአችሁና ወደ ፍርድ ቤት የሚጐትቷችሁስ ሀብታሞች አይደሉምን?