ምሳሌ 6:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተ ሰነፍ ወደ ጒንዳን ሄደህ መንገድዋን ተመልክተህ ጥበብን ቅሰም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንተ ሰነፍ፤ ወደ ጕንዳን ሂድ፤ ዘዴውን አስተውለህ ጠቢብ ሁን፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተ ሰነፍ፥ ወደ ገብረ ጉንዳን ሂድ፥ መንገድዋንም ተመልክተህ ጠቢብ ሁን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተ ታካች፥ ወደ ገብረ ጕንዳን ሂድ፥ መንገዱንም ተመልክተህ ቅና። ከእርሱም ይልቅ ብልህ ሁን። |
ሽመላዎች እንኳ የሚመለሱበትን ጊዜ ያውቃሉ፤ ዋኖሶች፥ ጨረባዎች፥ ዋርዳዎችም በኅብረት የሚሰደዱበትን ጊዜ ያውቃሉ፤ እናንተ ሕዝቤ ግን እንድትተዳደሩበት የሰጠኋችሁን ሕግ አታውቁም።
እስቲ በሰማይ ላይ ወደሚበሩት ወፎች ተመልከቱ፤ እነርሱ አይዘሩም፤ አያጭዱም፤ በጐተራ አይከቱም፤ ነገር ግን የሰማዩ አባታችሁ ይመግባቸዋል። ታዲያ እናንተ ከወፎች እጅግ ትበልጡ የለምን?