Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ምሳሌ 6:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 አንተ ሰነፍ፤ ወደ ጕንዳን ሂድ፤ ዘዴውን አስተውለህ ጠቢብ ሁን፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 አንተ ሰነፍ፥ ወደ ገብረ ጉንዳን ሂድ፥ መንገድዋንም ተመልክተህ ጠቢብ ሁን።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 አንተ ሰነፍ ወደ ጒንዳን ሄደህ መንገድዋን ተመልክተህ ጥበብን ቅሰም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 አንተ ታካች፥ ወደ ገብረ ጕንዳን ሂድ፥ መንገዱንም ተመልክተህ ቅና። ከእርሱም ይልቅ ብልህ ሁን።

Ver Capítulo Copiar




ምሳሌ 6:6
24 Referencias Cruzadas  

ሰነፍ ሰው በወቅቱ አያርስም፤ ስለዚህ በመከር ወራት ይፈልጋል፤ አንዳችም አያገኝም።


ለሥራው ደንታ የሌለው ሰው፣ የአጥፊ ወንድም ነው።


አንተ ሰነፍ፤ እስከ መቼ ትተኛለህ? ከእንቅልፍህስ መቼ ትነሣለህ?


በእምነትና በትዕግሥት የተስፋውን ቃል የሚወርሱትን እንድትመስሉ እንጂ ዳተኞች እንድትሆኑ አንፈልግም።


ሰነፍ አጥብቆ ይመኛል፤ አንዳችም አያገኝም፤ የትጉሆች ምኞት ግን ይረካል።


“ጌታውም መልሶ፣ ‘አንተ ክፉ፣ ሰነፍ ባሪያ፤ ካልዘራሁበት የማጭድ፣ ካልበተንሁበትም የምሰበስብ መሆኔን ታውቅ ኖሯል?


ጕንዳኖች ደካማ ፍጥረታት ናቸው፤ ሆኖም ምግባቸውን በበጋ ያከማቻሉ።


ጌታን ለማገልገል በመንፈስ የጋላችሁ ሁኑ እንጂ ከዚህ ትጋት ወደ ኋላ አትበሉ።


ሰነፍን የሚገድለው ምኞቱ ነው፤ እጆቹ መሥራት አይፈልጉምና።


ስንፍና ከባድ እንቅልፍ ላይ ይጥላል፤ ዋልጌም ሰው ይራባል።


ሰነፍ፣ “አንበሳ በውጭ አለ፤ በጐዳና ላይ እገደላለሁ” ይላል።


ሖምጣጤ ጥርስን፣ ጢስ ዐይንን እንደሚጐዳ፣ ሰነፍም ለሚልኩት እንዲሁ ነው።


ሰነፍ እጁን ወጭት ውስጥ ያጠልቃል፤ ወደ አፉ ግን መመለስ እንኳ ይሳነዋል።


እስኪ የሰማይ ወፎችን ተመልከቱ፤ አይዘሩም፤ አያጭዱም፤ በጐተራም አያከማቹም፤ ይሁን እንጂ የሰማዩ አባታችሁ ይመግባቸዋል። እናንተ ከእነርሱ እጅግ አትበልጡምን?


የሰነፍ መንገድ በእሾኽ የታጠረች ናት፤ የቅኖች መንገድ ግን የተጠረገ አውራ ጐዳና ነው።


ወፎች ፊት እያዩ ወጥመድ መዘርጋት፣ ምንኛ ከንቱ ነው!


በሬ ጌታውን፣ አህያ የባለቤቱን ጋጥ ያውቃል፤ እስራኤል ግን አላወቀም፤ ሕዝቤም አላስተዋለም።”


ልጄ ሆይ አድምጥ፤ ጠቢብም ሁን፤ ልብህም ከትክክለኛው መንገድ አይውጣ።


“በምድር ላይ አራት ነገሮች ትንንሽ ናቸው፤ ሆኖም እጅግ ጠቢባን ናቸው፤


ሽመላ እንኳ በሰማይ፣ የተወሰነ ጊዜዋን ታውቃለች፤ ዋኖስ፣ ጨረባና ዋርዳም፣ የሚሰደዱበትን ጊዜ ያውቃሉ፤ ሕዝቤ ግን፣ የእግዚአብሔርን ሥርዐት አላወቀም።


ሰነፍ እጆች ሰውን ያደኸያሉ፤ ትጉህ እጆች ግን ብልጽግናን ያመጣሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios