ምሳሌ 22:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በክፉዎች መንገድ ላይ እሾኽና ወጥመድ አለ፤ ራሱን የሚጠብቅ ግን ከእነርሱ ይርቃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በክፉዎች መንገድ ላይ እሾኽና ወጥመድ አለ፤ ነፍሱን የሚጠብቅ ግን ከእነዚህ ይርቃል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እሾህና ወጥመድ በጠማማ ሰው መንገድ ላይ ይገኛሉ፥ ነፍሱን ግን የሚጠብቅ ከእነርሱ ይርቃል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እሾህና ወጥመድ በጠማማ ሰው መንገድ ናቸው፤ ነፍሱን የሚጠብቅ ግን ከእነርሱ ያመልጣል። |
አምላካችሁ እግዚአብሔር እነዚህን ሕዝቦች ከፊታችሁ ማባረሩን እንደማይቀጥል በእርግጥ ዕወቁ፤ እንዲያውም አምላካችሁ እግዚአብሔር ከሰጣችሁ ከዚህች መልካም ምድር እስክትጠፉ ድረስ እነዚህን ሕዝቦች ለጀርባችሁ መግረፊያ፥ ለዐይኖቻችሁ እንደሚወጋ እሾኽ፥ እንዲሁም አደገኛ ወጥመድና መውደቂያ ጒድጓድ ይሆኑባችኋል።