Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢዮብ 18:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 በገዛ ራሱ እርምጃ አሽክላ ውስጥ ይገባል፤ እግሩም በመረቡ ውስጥ ይተበተባል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 እግሩ በወጥመድ ይያዛል፤ በመረብም ይተበተባል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 እግሩ በወጥመድ ትያዛለች፥ በመረብም ላይ ይሄዳል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 እግሩ በወ​ጥ​መድ ትያ​ዛ​ለች፤ በመ​ረ​ብም ትታ​ሠ​ራ​ለች፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 እግሩ በወጥመድ ትያዛለች፥ በመረብም ላይ ይሄዳል።

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 18:8
18 Referencias Cruzadas  

ንጉሥ ሆይ! ይህ ሕዝብ በሞት የሚቀጣበትን ዐዋጅ ለማስተላለፍ መልካም ፈቃድህ ይሁን፤ ይህን ብታደርግ እኔ ለንጉሠ ነገሥት መንግሥትህ አስተዳደር መርጃ ይሆን ዘንድ ሦስት መቶ አርባ ሺህ ኪሎ የሚመዝን ብር ወደ መንግሥት ግምጃ ቤት ገቢ እንደማደርግ ቃል እገባለሁ።”


ለሚስቱና ለወዳጆቹም የደረሰበትን አሳፋሪ ነገር በሙሉ ነገራቸው፤ ሚስቱና እነዚያ አስተዋዮች የሆኑ ወዳጆቹም “እነሆ በገዛ እጅህ ሥልጣንህን ለመርዶክዮስ ልታስረክብ ተቃርበሃል፤ እርሱ አይሁዳዊ ስለ ሆነ ልትቋቋመው አትችልም፤ በእርግጥም እርሱ ያሸንፍሃል!” አሉት።


ስለዚህም ሃማን መርዶክዮስን ለመስቀል ባዘጋጀው እንጨት ላይ ተሰቀለ፤ ከዚያም በኋላ የንጉሡ ቊጣ በረደ።


ከዚህም በኋላ ንጉሥ አርጤክስስ “ይህን ለማድረግ የደፈረ ማን ነው? ለመሆኑ ይህ ሰው የት ይገኛል?” ሲል ንግሥት አስቴርን ጠየቃት።


አሽክላ ተረከዙን ይይዘዋል፤ ወጥመድም አጣብቆ ያስቀረዋል።


ነገር ግን ይህን ሁሉ መከራ ያደረሰብኝና መረብ ውስጥም የጣለኝ እግዚአብሔር መሆኑን እንድታውቁ እወዳለሁ።


በዚህም ምክንያት እነሆ፥ ዙሪያህን በወጥመድ ተከበሃል፤ ድንገተኛ አደጋም ያሸብርሃል፤


ሰብሉንም የተራቡ ሰዎች ይበሉታል፤ በእሾኽ መካከል የበቀለውን እንኳ አይተውለትም፤ የተጠሙ ሰዎችም ሀብቱን ለመውሰድ ይጐመዣሉ።


ያላሰቡት ድንገተኛ ጥፋት ይድረስባቸው፤ የደበቁት ወጥመድ ይያዛቸው በቈፈሩትም ጒድጓድ ወድቀው ይጥፉ!


አሕዛብ በቈፈሩት ጒድጓድ ወደቁ፤ በደበቁት ወጥመድ ተያዙ።


ክፉ ሰው የገዛ ኃጢአቱ ወጥመድ ሆኖ ይይዘዋል፥ ደግ ሰው ግን እየዘመረ ሐሤትን ያደርጋል።


ኃጢአተኛን ሰው የገዛ ራሱ ክፋት ያጠምደዋል፤ በኃጢአቱም ገመድ ይታሰራል።


በምድር ላይ የምትኖሩ ሁሉ! አድምጡኝ! ሽብር፥ ጒድጓድና ወጥመድ ይጠብቃችኋል።


ከአሸባሪ ድምፅ የሚሸሽ በተቈፈረ ጒድጓድ ውስጥ ይወድቃል፤ ከጒድጓድ ዘሎ ለማምለጥ የሚሞክርም በወጥመድ ይያዛል፤ ከሰማይ ብርቱ ዝናብ ይዘንባል፤ የምድር መሠረቶችም ይናወጣሉ።


ብዙ አሕዛብ በሚሰበሰቡበት ጊዜ መረቤን እዘረጋብሃለሁ፤ በእኔ መረብ መሳቢያም ጐትተው ወደ ዳር እንዲያወጡህ አደርጋለሁ።


በነቀፋና በሰይጣን ወጥመድ ውስጥ እንዳይወድቅ በማያምኑ ሰዎች ዘንድ መልካም ስም እንዲኖረው ያስፈልጋል።


ሀብታሞች ለመሆን የሚፈልጉ ግን በፈተና ይወድቃሉ፤ ሰዎችን በሚያበላሽና በሚያጠፋ ከንቱና አደገኛ በሆነ በብዙ ምኞት ወጥመድ ይያዛሉ።


በዚህ ዐይነት ወደ ልቡናቸው ተመልሰው ዲያብሎስ ፈቃዱን እንዲፈጽሙ እነርሱን ከያዘበት ወጥመድ ያመልጣሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos