ምሳሌ 22:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዘወትር ብታስታውሳቸውና ብትጠቀምባቸው ደስ ይሉሃል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በልብህ ስትጠብቃቸው፣ ሁሉም በከንፈሮችህ ላይ የተዘጋጁ ሲሆኑ ደስ ይላልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱን በውስጥህ ብትጠብቅ፥ በከንፈሮችህም ላይ የተዘጋጁ ቢሆኑ፥ አስደሳች ነገር ይሆንልሃልና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱን በልብህ ብትጠብቅ፥ በከንፈሮችህ በአንድነት ደስ ያሰኙሃል። |
የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! እኔ በስምህ ተጠርቼአለሁ፤ ቃልህ ወደ እኔ በመጣ ጊዜ በሙሉ ተቀብዬዋለሁ፤ ልቤንም በደስታና በሐሴት ሞላው።
እንግዲህ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት የምስጋና መሥዋዕት ዘወትር ለእግዚአብሔር እናቅርብ፤ ይህም ስለ ስሙ በሚመሰክሩት ከንፈሮች የሚቀርብ የምስጋና መሥዋዕት ነው።