Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ምሳሌ 25:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 በወቅቱ በትክክል የተነገረ ቃል በብር ጻሕል ላይ እንደ ተቀመጠ ወርቅ ውበት ይኖረዋል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ባግባቡ የተነገረ ቃል፣ በብር መደብ ላይ እንደ ተቀረጸ የወርቅ እንኮይ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 በአግባብ የተነገረ ቃል፥ በብር ፃሕል ላይ እንደተቀመጠ ወርቅ ነው።

Ver Capítulo Copiar




ምሳሌ 25:11
8 Referencias Cruzadas  

ቃሎችህ የሚሰናከሉትን ይደግፉ ነበር፤ የሚብረከረኩትንም ጒልበቶች ታበረታ ነበር።


ተገቢውን ቃል በተገቢው ቦታ መናገር እጅግ ያስደስታል።


ትክክለኛ መልስ የሚሰጥ ሰው እንደ ልብ ወዳጅ ይቈጠራል።


አለበለዚያ ምሥጢር የማትጠብቅ መሆንክን የሚያውቅ ሰው ያዋርድሃል፤ ሊለወጥ የማይችልም መጥፎ ስም ይሰጥሃል።


ጥበበኛው ተስማሚ የሆኑ ቃላትንም መረመረ፤ ስለዚህ እርሱ የጻፈው ሁሉ እውነትና ትክክል ነው።


ደካሞችን በቃል ማጽናትን ዐውቅ ዘንድ ጌታ እግዚአብሔር የምሁርን አንደበት ሰጥቶኛል፤ በየማለዳው ከእንቅልፍ ያነቃኛል፤ እንደ ተማሪም አዳምጥ ዘንድ ጆሮዬን ይከፍታል።


“መልካም ሰው ከመልካም መዝገቡ፥ መልካም ነገርን ያወጣል፤ ክፉ ሰውም ከክፉ መዝገቡ ክፉ ነገርን ያወጣል።


ከዚያም በኋላ ዳዊት ያመጣችለትን ስጦታ ተቀብሎ “ወደ ቤትሽ በሰላም ተመልሰሽ ሂጂ፤ ልመናሽን ሰምቼአለሁ፤ የጠየቅሽውን ሁሉ አደርጋለሁ” አላት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos