ከዚህም የተነሣ በአብራም እረኞችና በሎጥ እረኞች መካከል ጠብ ተነሣ፤ በዚያን ዘመን የዚያች ምድር ነዋሪዎች ከነዓናውያንና ፈሪዛውያን ነበሩ።
ምሳሌ 20:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ማንኛውም ሞኝ ተቈጥቶ ጠብ ማነሣሣት ይችላል፤ ሰውን የሚያስከብረው ግን ከክርክር መራቅ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከጠብ መራቅ ለሰው ክብሩ ነው፤ ቂል ሁሉ ግን ለጥል ይቸኵላል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከክርክር ይርቅ ዘንድ ለሰው ክብሩ ነው፥ ሰነፍ ሁሉ ግን እንዲህ ባለ ነገር ይጣመራል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሰው ክብሩ ከስድብ መከልከል ነው፤ ሰነፍ ሁሉ ግን እንዲህ ባለ ነገር ይጣመራል። |
ከዚህም የተነሣ በአብራም እረኞችና በሎጥ እረኞች መካከል ጠብ ተነሣ፤ በዚያን ዘመን የዚያች ምድር ነዋሪዎች ከነዓናውያንና ፈሪዛውያን ነበሩ።
ከዚህ በኋላ አብራም ሎጥን እንዲህ አለው፤ “እኛ ወንድማማች ስለ ሆንን በእኔና በአንተ መካከል እንዲሁም በእኔ እረኞችና በአንተ እረኞች መካከል ጠብ ሊነሣ አይገባም፤
ንጉሥ ዮአስ ግን እንዲህ ሲል መለሰለት “አንድ ጊዜ በሊባኖስ ተራራ ላይ የምትገኝ ኲርንችት የሊባኖስ ዛፍ ‘ለወንድ ልጄ ሚስት ትሆነው ዘንድ ሴት ልጅህን ስጠኝ’ ስትል መልእክት ላከችበት፤ ነገር ግን አንድ የሊባኖስ አውሬ እግረ መንገዱን በዚያ ሲያልፍ ስለ ረገጣት ያቺ ኲርንችት ሞተች፤
ይልቅስ እርስ በርሳችሁ ደጎችና አዛኞች ቸሮችና ርኅሩኆች ሁኑ፤ እግዚአብሔር በክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ እናንተም እርስ በርሳችሁ ይቅር ተባባሉ።