2 ነገሥት 14:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 ንጉሥ ዮአስ ግን እንዲህ ሲል መለሰለት “አንድ ጊዜ በሊባኖስ ተራራ ላይ የምትገኝ ኲርንችት የሊባኖስ ዛፍ ‘ለወንድ ልጄ ሚስት ትሆነው ዘንድ ሴት ልጅህን ስጠኝ’ ስትል መልእክት ላከችበት፤ ነገር ግን አንድ የሊባኖስ አውሬ እግረ መንገዱን በዚያ ሲያልፍ ስለ ረገጣት ያቺ ኲርንችት ሞተች፤ Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም9 የእስራኤል ንጉሥ ዮአስ ግን ለይሁዳ ንጉሥ ለአሜስያስ እንዲህ ሲል ላከበት፤ “አንድ የሊባኖስ ኵርንችት፣ ለአንድ የሊባኖስ ዝግባ፣ ‘ሴት ልጅህን ለልጄ ሚስት እንድትሆነው ስጠው’ አለው፤ ከዚያም አንድ የሊባኖስ ዱር አውሬ መጥቶ ኵርንችቱን በእግሩ ረገጠው። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 ንጉሥ ዮአስ ግን እንዲህ ሲል መለሰለት “አንድ ጊዜ በሊባኖስ ተራራ ላይ የምትገኝ ኲርንችት የሊባኖስ ዛፍ ‘ለወንድ ልጄ ሚስት ትሆነው ዘንድ ሴት ልጅህን ስጠኝ’ ስትል መልእክት ላከችበት፤ ነገር ግን አንድ የሊባኖስ አውሬ እግረ መንገዱን በዚያ ሲያልፍ ስለ ረገጣት ያቺ ኲርንችት ሞተች፤ Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 የእስራኤልም ንጉሥ ዮአስ፥ “የሊባኖስ ኵርንችት፦ ልጅህን ለልጄ ሚስት አድርገህ ስጠው ብሎ ወደ ሊባኖስ ዝግባ ላከ፤ የሊባኖስም አውሬ አልፎ ኵርንችቱን ረገጠ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 የእስራኤልም ንጉሥ ዮአስ “የሊባኖስ ኵርንችት፥ ‘ልጅህን ለልጄ ሚስት አድርገህ ስጠው፤’ ብሎ ወደ ሊባኖስ ዝግባ ላከ፤ የሊባኖስም አውሬ አልፎ ኵርንችቱን ረገጠ። Ver Capítulo |