La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ምሳሌ 18:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የሞኝ ንግግር ጠብን ያነሣሣል፤ ልፍለፋውም በትርን ይጋብዛል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የሞኝ ከንፈር ጠብ ያመጣበታል፤ አፉም በትር ይጋብዛል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የሰነፍ ከንፈር በጥል ውስጥ ትገባለች፥ አፉም በትርን ትጠራለች።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አላዋቂን ከንፈሮቹ ወደ ክፉ ያደርሱታል፥ የችኩል አፍም ሞትን ይጠራል።

Ver Capítulo



ምሳሌ 18:6
14 Referencias Cruzadas  

የሞኝ ቊጣ ወዲያው ይታወቃል፤ ብልኅ ሰው ግን በእርሱ ላይ የተሰነዘረውን ስድብ ችላ ይላል።


ትዕቢት ጠብን ያመጣል፤ ምክርን መጠየቅ ግን ብልኅነት ነው።


ብልኆች እግዚአብሔርን ስለሚፈሩ ከክፉ ነገር ለመራቅ ይጠነቀቃሉ፤ ሞኞች ግን ከአደጋ የማይጠነቀቁ ችኲሎች ናቸው።


ሞኝን የገዛ ንግግሩ ያስቀጣዋል፤ ጥበበኞችን ግን መልካም አነጋገራቸው ይጠብቃቸዋል።


የጥል መነሻ መፍረስ እንደ ጀመረ ግድብ ነው፤ ስለዚህ ጥል ከማስከተሉ በፊት ክርክርን አቁም።


ግልፍተኛ ሰው ቢኖር የግልፍተኛነቱን ዋጋ እንዲያገኝ ተወው፤ አንድ ጊዜ ከችግሩ ልታወጣው ብትሞክር ሌላ ጊዜም እንዲሁ ማድረግህ አይቀርም።


ለፌዘኞች ፍርድ፥ ለሞኞችም ግርፋት ተዘጋጅቶላቸዋል።


ማንኛውም ሞኝ ተቈጥቶ ጠብ ማነሣሣት ይችላል፤ ሰውን የሚያስከብረው ግን ከክርክር መራቅ ነው።


ፌዘኛን ሰው ብታስወጣ ጠብ ይቆማል፤ ጠብና ስድብም አይኖሩም።


ከጨቅጫቃ ሚስት ጋር በአንድ ቤት ከመኖር ይልቅ በጣራ ማእዘን ላይ መኖር ይሻላል።


ድንጋይና አሸዋ ከባድ ናቸው፤ ሞኝ ሰው የሚያነሣሣው ቊጣ ግን ከሁለቱም ይከብዳል።


ጥበበኛ ሰው ሞኝን ሰው ከሶ ፍርድ ቤት ቢያቀርብ ሞኙ ሰው በቊጣና በሳቅ ሰላምን ይነሣል።