መሪዎቹ መኖሪያቸውን በኢየሩሳሌም አደረጉ፤ ከሌላውም ሕዝብ መካከል ከየዐሥር ቤተሰብ አንዱ እጅ ቅድስት በሆነችው በኢየሩሳሌም ከተማ እንዲኖር በዕጣ ተመረጠ፤ የቀሩት ሰዎች ግን በሌሎች መንደሮችና ከተሞች ሁሉ ኑሮአቸውን መሠረቱ፤
ምሳሌ 16:33 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰዎች የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማወቅ ዕጣ ይጥላሉ፤ ነገር ግን ውሳኔውን የሚሰጠው እግዚአብሔር ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዕጣ በጕያ ውስጥ ይጣላል፤ ውሳኔው በሙሉ ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዕጣ በጉያ ይጣላል፥ መደብዋ ሁሉ ግን ከጌታ ዘንድ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የበደለኛ ሰው በደሉ ሁሉ ወደ ጕያው ይመለሳል። ጽድቅ ሁሉ ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው። |
መሪዎቹ መኖሪያቸውን በኢየሩሳሌም አደረጉ፤ ከሌላውም ሕዝብ መካከል ከየዐሥር ቤተሰብ አንዱ እጅ ቅድስት በሆነችው በኢየሩሳሌም ከተማ እንዲኖር በዕጣ ተመረጠ፤ የቀሩት ሰዎች ግን በሌሎች መንደሮችና ከተሞች ሁሉ ኑሮአቸውን መሠረቱ፤
የባቢሎን ንጉሥ በመስቀለኛ መንገዶቹ መታጠፊያ አጠገብ ይቆማል፤ በየትኛው መንገድ መሄድ እንዳለበት ለማወቅ ፍላጻዎችን ይወረውራል፤ ጣዖቶቹንም ምክር ይጠይቃል፤ ለመሥዋዕት ከታረደ እንስሳ የጒበት ሞራ ወስዶም ይመረምራል።
በመርከቢቱ ውስጥ የነበሩትም ሁሉ እርስ በርሳቸው “በዚህ አደጋ ላይ እንድንወድቅ ምክንያት የሆነው ማን እንደ ሆነ ለማወቅ ኑ ዕጣ እንጣጣል” ተባባሉ። ዕጣም ተጣጣሉ፤ ዕጣውም በዮናስ ላይ ወጣ።
እነርሱም የሚያጠኑት ምድር ለሰባቱ ነገድ ይከፋፈላል፤ ይሁዳ በደቡብ በኩል፥ ዮሴፍም በሰሜን በኩል የተመደበላቸውን የርስት ድርሻ ይዘው ይኖራሉ፤
ስለዚህ ነገ ጧት በየነገዳችሁ ቅረቡ፤ እግዚአብሔር የሚለየው ነገድ በየጐሣው ይቅረብ፤ እግዚአብሔር የሚለየው ጐሣ በየቤተሰቡ ይቅረብ፤ እግዚአብሔር የሚለየው ቤተሰብ በየግለሰቡ ይቅረብ፤
ዛሬ ግን ከመከራችሁና ከጭንቀታችሁ ያዳናችሁን አምላካችሁን ትታችኋል፤ እናንተም፦ ‘አይሆንም ንጉሥ አንግሥልን’ አላችሁት። አላችሁት። ስለዚህ አሁን በየነገዳችሁና በየወገናችሁ ወደ እግዚአብሔር ፊት ቅረቡ”።