Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ምሳሌ 18:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ዕጣ መጣል ጠብን ያበርዳል፤ ሁለት ጠንካራ ተከራካሪዎችንም ይገላግላል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ዕጣ መጣጣል ሙግትን ያስቆማል፤ ኀይለኛ ባላንጣዎችንም ይገላግላል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ዕጣ ክርክርን ትከለክላለች፥ በኃያላንም መካከል ትበይናለች።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ዕጣ ክርክርን ያስተዋል፥ በኀያላንም መካከል ይለያል።

Ver Capítulo Copiar




ምሳሌ 18:18
10 Referencias Cruzadas  

ሰዎች የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማወቅ ዕጣ ይጥላሉ፤ ነገር ግን ውሳኔውን የሚሰጠው እግዚአብሔር ነው።


መሪዎቹ መኖሪያቸውን በኢየሩሳሌም አደረጉ፤ ከሌላውም ሕዝብ መካከል ከየዐሥር ቤተሰብ አንዱ እጅ ቅድስት በሆነችው በኢየሩሳሌም ከተማ እንዲኖር በዕጣ ተመረጠ፤ የቀሩት ሰዎች ግን በሌሎች መንደሮችና ከተሞች ሁሉ ኑሮአቸውን መሠረቱ፤


የእያንዳንዱ ቤተሰብ አለቃና ታናሹ እንደ ታላቁ በእኩልነት ልክ ዘመዶቻቸው የአሮን ልጆች የነበሩት ካህናት ያደርጉት በነበረው ዐይነት ለሥራቸው ምድብ ዕጣ ይጥሉ ነበር፤ ንጉሥ ዳዊት፥ ሳዶቅ፥ አቤሜሌክና የካህናትና የሌዋውያን ቤተሰቦች አለቆች ሁሉ በተገኙበት ዕጣ ተጣጥለዋል።


እንዲሁም ለመራሪ ጐሣ በየወገናቸው ከሮቤል፥ ከጋድና ከዛብሎን ግዛቶች በአጠቃላይ ዐሥራ ሁለት ከተሞች በዕጣ ተመድበው ነበር።


ከዚህም በኋላ ሳኦል “በእኔና በልጄ በዮናታን መካከል ዕጣ ጣሉ” አለ፤ ዕጣውም በዮናታን ላይ መጣ፤


እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተምዕራብ ያለው ግዛት በሙሉ ለዘጠኙ ነገድ ተኩል በዕጣ ተከፈለ።


በአደባባይ በመጀመሪያ ቀርቦ የሚናገር ሰው ተከራካሪው መጥቶ ጥያቄ እስከሚያቀርብለት ድረስ፥ ዘወትር እርሱ ብቻ ትክክል የሆነ ይመስለዋል።


ወንድምህን እርዳው፤ እርሱም በከተማ ዙሪያ እንዳለ ጠንካራ ግንብ ይጠብቅሃል፤ ከእርሱ ጋር ብትጣላ ግን በሩን ይዘጋብሃል።


ሳኦልም ወደ እስራኤል አምላክ ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ጸለየ፤ “እግዚአብሔር ሆይ! ዛሬ ስለምን መልስ አልሰጠኸኝም? የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! በእነዚህ በተቀደሱ ድንጋዮች አማካይነት መልስ ስጠኝ፤ ይህን በደል የሠራነው ዮናታን ወይም እኔ ከሆንን በኡሪም አማካይነት፥ ይህን በደል የፈጸሙ ሕዝብህ እስራኤል ከሆኑ በቱሚም አማካይነት መልስ ስጠኝ።” መልሱም ዮናታንንና ሳኦልን ስላመለከተ ሕዝቡ ነጻ ሆኑ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios