ዘኍል 29:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህንንም ሁሉ መሥዋዕት በየወሩ መጀመሪያ ቀን ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕትና የእህል ቊርባን፥ እንዲሁም በየቀኑ ከሚቀርበው መዓዛው እግዚአብሔርን ደስ ከሚያሰኝ የሚቃጠል መሥዋዕት የእህል ቊርባንና የመጠጥ መባ ጋር ተጨማሪ በማድረግ ታቀርባላችሁ፤ ይህም የምግብ ቊርባን ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነዚህ እንግዲህ በተደነገገው መሠረት ከእህል ቍርባናቸውና ከመጠጥ ቍርባናቸው ጋራ በየዕለቱና በየወሩ ከሚቀርቡት የሚቃጠሉ መሥዋዕቶች ሌላ ተጨማሪ ሆነው፣ ለእግዚአብሔር ሽታቸው ደስ የሚያሰኝ በእሳት የሚቀርቡ መሥዋዕቶች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በወሩ መባቻ ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከእህሉ ቁርባን፥ ዘወትርም ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከእህሉ ቁርባን፥ ከመጠጡም ቁርባን ሌላ፥ እንደ ሕጋቸው ለጌታ መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን በእሳት የሚቀርቡ ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በወሩ መባቻ ከሚቃጠለው መሥዋዕት ሌላ ከእህሉ ቍርባን፥ ከመጠጡም ቍርባን እንደ ሕጋቸው ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ እንዲሆን በእሳት የሚቀርቡ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በወሩ መባቻ ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከእህሉ ቍርባን፥ በዘወትርም ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከእህሉ ቍርባን፥ ከመጠጡም ቍርባን ሌላ፥ እንደ ሕጋቸው ለእግዚአብሔር ጣፋጭ ሽታ እንዲሆን በእሳት የሚቀርቡ ናቸው። |
“ለአሮንና ለልጆቹ የምትሰጣቸው የሥርዓት መመሪያ ይህ ነው፤ የሚቃጠል መሥዋዕት ሌሊቱን ሁሉ በመሠዊያው ላይ እንዲቈይ ተደርጎ እሳቱ ሲነድ ይደር፤
እንዲህ ዐይነቱ ስሕተት የተፈጸመው በማኅበሩ አለማወቅ ከሆነ አንድ ወይፈን አምጥተው መዓዛው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገው ያቅርቡት፤ ከእርሱም ጋር ተገቢውን የእህልና የወይን ጠጅ ቊርባን ያቅርቡ፤ በተጨማሪም አንድ ተባዕት ፍየል ስለ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት አድርገው ያቅርቡ።
እንግዲህ እንደዚህ ያለውን መሥዋዕት የሚያቀርብ ሰው ሁሉ በሩብ ሊትር ዘይት የተለወሰ አንድ ኪሎ ምርጥ ዱቄት የእህል ቊርባንም ማቅረብ አለበት፤
ሁለት ወይፈኖች፥ አንድ አውራ በግ፥ አንድ ዓመት የሞላቸው ሰባት ተባዕት የበግ ጠቦቶች፥ መዓዛው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ።
ያቀረባቸውም መባዎች እነዚህ ናቸው፦ በመቅደሱ ሚዛን መሠረት መቶ ሠላሳ ሰቅል የሚመዝን አንድ ከብር የተሠራ ዝርግ ሳሕን፥ ከሰባ ሰቅል ብር የተሠራ አንድ ጐድጓዳ ሳሕን፥ ሁለቱም ለእህል ቊርባን በሚሆን ከዘይት ጋር በተቀላቀለ ደቃቅ ዱቄት የተሞሉ፥
“በእናንተ መካከል መጻተኛ የእግዚአብሔርን ፋሲካ በዓል ለማክበር ቢፈልግ በተወሰነው ደንብና የሥርዓት መመሪያ ሁሉ መሠረት ማክበር ይኖርበታል፤ የአገር ተወላጁም ሆነ መጻተኛ ይህን ደንብ በተመሳሳይ ሁኔታ ይፈጽም።”