Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዕዝራ 3:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ሕጉም በሚያዘው መሠረት የዳስ በዓልን አከበሩ፤ ለእያንዳንዱም ቀን የተመደበውን መሥዋዕት አቀረቡ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ከዚያም ለእያንዳንዱ ቀን እንደ ታዘዘው፣ በሚያስፈልገው ቍጥር ልክ የሚቃጠል መሥዋዕት በማቅረብ የዳስ በዓልን በተጻፈው መሠረት አከበሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 እንደተጻፈውም የዳስ በዓል አከበሩ፤ እንደ ሥርዓቱም የዕለቱን የሚቃጠል መሥዋዕት በዕለቱ በቍጥር አቀረቡ፤ የዕለቱን ነገር በዕለቱ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 እንደ ተጻ​ፈ​ውም የዳስ በዓል አደ​ረጉ፤ እንደ ሥር​ዐ​ቱም ለየ​ዕ​ለቱ የተ​ገ​ባ​ውን የየ​ዕ​ለ​ቱን የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት በቍ​ጥር አቀ​ረቡ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 እንደተጻፈውም የዳስ በዓል አደረጉ፤ እንደ ሥርዓቱም ለየዕለቱ የተገባውን የየዕለቱን የሚቃጠል መሥዋዕት በቍጥር አቀረቡ።

Ver Capítulo Copiar




ዕዝራ 3:4
14 Referencias Cruzadas  

ንጉሥ ዳዊት አሳፍንና ሌዋውያን የሆኑትን ወገኖቹን የቃል ኪዳኑ ታቦት ባለበት ስፍራ ለሚካሄደው የአምልኮ ሥነ ሥርዓት ለዘለቄታው ኀላፊዎች እንዲሆኑ አደረጋቸው፤ በዚያም አገልግሎታቸውን በየቀኑ ይፈጽሙ ነበር፤


በተጨማሪም በተለያዩ የየዕለት ተግባራቸው ወደ ቤተ መቅደስ ለሚገቡ ከሦስት ዓመት ዕድሜ በላይ ላላቸው ወንዶች እንደየ ኀላፊነታቸውና እንደየምድባቸው ድርሻ ድርሻቸውን ያከፋፍሉ ነበር፤


“የምድራችሁን ሰብል በምትሰበስቡበት ጊዜ የመከር በዓል አክብሩ፤ “ከወይን ተክሎቻችሁና ከፍራፍሬ ዛፎቻችሁ ፍሬ በምትሰበስቡበት ጊዜ በዓመቱ መጨረሻ የዳስ በዓል አክብሩ፤


“በሚመጡት ዘመናት ሁሉ በየዕለቱ አንድ ዓመት የሆናቸው ሁለት ጠቦቶች መሥዋዕት አድርገህ በመሠዊያው ላይ ታቀርባለህ፤


ጨካኞች የሆኑትም አሠሪዎች ቀድሞ ገለባ እየሰጡአቸው ይሠሩት የነበረውን ያኽል ጡብ ቈጥረው እንዲያስረክቡ ያስገድዱአቸው ጀመር።


በሚኖርበት ዘመን ሁሉ በየቀኑ ለማናቸውም ለሚያስፈልገው ነገር ያውለው ዘንድ የዘወትር አበል ይሰጠው ነበር።


እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ አለው፦


“በተወሰኑላችሁ በዓሎች እነዚህን ለጌታ ታቀርባላችሁ፤ ይህም ከስእለት ቊርባናችሁ፥ በፈቃዳችሁ ከምታቀርቡት መባ ሌላ የሚቃጠል መሥዋዕታችሁን፥ የእህል ቊርባናችሁን፥ የመጠጥ ቊርባናችሁንና የአንድነት ቊርባናችሁን ታቀርባላችሁ።”


በዚያን ጊዜ የአይሁድ የዳስ በዓል ቀርቦ ነበር።


የበዓሉ መጨረሻ በሆነው በታላቁ ቀን ኢየሱስ ቆመና ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ አለ፦ “ውሃ የጠማው ቢኖር ወደ እኔ መጥቶ ይጠጣ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos