ዘኍል 15:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም4 እንግዲህ እንደዚህ ያለውን መሥዋዕት የሚያቀርብ ሰው ሁሉ በሩብ ሊትር ዘይት የተለወሰ አንድ ኪሎ ምርጥ ዱቄት የእህል ቊርባንም ማቅረብ አለበት፤ Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም4 መሥዋዕቱን ይዞ የሚመጣው ሰው በሂን አንድ አራተኛ ዘይት የተለወሰ የኢፍ አንድ ዐሥረኛ የላመ ዱቄት የእህል ቍርባን ለእግዚአብሔር ያቀርባል። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)4 ቁርባኑን ለማቅረብ የሚያመጣ ሰው የኢን መስፈሪያ አራተኛ እጅ በሆነ ዘይት የተለወሰ ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ አንድ እጅ የሆነ መልካም ዱቄትን የእህል ቁርባን አድርጎ ለጌታ ያቅርብ፤ Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)4 ቍርባኑን ለእግዚአብሔር የሚያቀርብ የኢፍ መስፈሪያ አራተኛ እጅ በሆነ ዘይት የተለወሰ የኢፍ መስፈሪያ ዐሥረኛ እጅ የሆነ የመልካም ዱቄት መሥዋዕት ያመጣል። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)4-5 ቍርባኑን ለእግዚአብሔር የሚያቀርብ ከሚቃጠል መሥዋዕት ወይም ከሌላ መሥዋዕት ጋር ለእያንዳንዱ ጠቦት የኢን መስፈሪያ አራተኛ እጅ በሆነ ዘይት የተለወሰ ከመስፈሪያው ከአሥር እጅ አንድ እጅ የሆነ መልካም ዱቄት ለእህል ቍርባን፥ የኢን መስፈሪያ አራተኛ እጅ የወይን ጠጅ ለመጠጥ ቍርባን ያዘጋጃል። Ver Capítulo |