በዚህ ዐይነት መላው እስራኤላውያን ጥሩምባና እምቢልታ እየነፉ፥ ጸናጽል እያንሿሹ፥ መሰንቆና በገና እየደረደሩ በሆታና በእልልታ የቃል ኪዳኑን ታቦት አጅበው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።
ዘኍል 29:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ሰባተኛው ወር በገባ በመጀመሪያው ቀን ለማምለክ ትሰበሰባላችሁ፤ በእርሱም ምንም ሥራ አትሠሩበትም፤ በዚያን ቀን መለከት ይነፋል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘በሰባተኛው ወር በመጀመሪያው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ አድርጉ፤ የዘወትር ሥራም አትሥሩበት፤ ይህም የመለከት ድምፅ የምታሰሙበት ቀናችሁ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሰባተኛውም ወር ከወሩ በመጀመሪያ ቀን የተቀደሰ ጉባኤ ይኑራችሁ፤ የጉልበት ሥራ ሁሉ አትሥሩበት፤ መለከቶች የሚነፉበት ቀን ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በሰባተኛውም ወር ከወሩ የመጀመሪያዋ ቀን ለእናንተ ይህች ዕለት የተቀደሰች ናት፤ የተግባርን ሥራ ሁሉ አትሥሩባት፤ ምልክት ያለባት ቀን ትሁንላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሰባተኛውም ወር ከወሩ በመጀመሪያ ቀን የተቀደሰ ጉባኤ ይሁንላችሁ፤ የተግባርን ሥራ ሁሉ አትሥሩበት፤ መለከቶች የሚነፉበት ቀን ነው። |
በዚህ ዐይነት መላው እስራኤላውያን ጥሩምባና እምቢልታ እየነፉ፥ ጸናጽል እያንሿሹ፥ መሰንቆና በገና እየደረደሩ በሆታና በእልልታ የቃል ኪዳኑን ታቦት አጅበው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።
እነርሱ የቤተ መቅደሱን ሕንጻ እንደገና መሥራት ባይጀምሩም እንኳ ሰባተኛው ወር በገባ በመጀመሪያው ቀን ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ማቅረባቸውን ጀመሩ።
ካህናቱ፥ ሌዋውያኑ፥ የቤተ መቅደስ ዘብ ጠባቂዎቹ፥ መዘምራኑ፥ ከሕዝቡም አንዳንድ ሰዎች የቤተ መቅደስ አገልጋዮች፥ በአጠቃላይ እስራኤላውያን ሁሉ በየከተሞቻቸው ሰፈሩ።
ስለዚህም ካህኑ ዕዝራ ሰባተኛው ወር በገባ በመጀመሪያው ቀን፥ ማስተዋል የሚችል ሕዝብ ሁሉ ሴት፥ ወንድ፥ ልጅ ዐዋቂው በሙሉ ወደተሰበሰቡበት ስፍራ፥ የሕጉን መጽሐፍ አመጣ፤
“የምድራችሁን ሰብል በምትሰበስቡበት ጊዜ የመከር በዓል አክብሩ፤ “ከወይን ተክሎቻችሁና ከፍራፍሬ ዛፎቻችሁ ፍሬ በምትሰበስቡበት ጊዜ በዓመቱ መጨረሻ የዳስ በዓል አክብሩ፤
በዚያም ዘመን ትልቅ መለከት ይነፋል፤ በአሦር ምድር ጠፍተው የነበሩትና ወደ ግብጽ ተሰደው የነበሩት እስራኤላውያንም ተመልሰው በኢየሩሳሌም በሚገኘው በተቀደሰው ተራራ ላይ ይሰግዳሉ።
እግዚአብሔር ከሕዝቡ በላይ ይገለጣል፤ የእርሱም ፍላጻዎች እንደ መብረቅ ይወረወራሉ፤ እግዚአብሔር አምላክ የመለከት ድምፅ ያሰማል፤ ከደቡብ በኩል እንደሚመጣ ዐውሎ ነፋስ ያልፋል።
“ሰባተኛው ወር በገባ በዐሥራ አምስተኛው ቀን በአንድነት ለማምለክ ትሰበሰባላችሁ፤ ይህንንም በዓል ለእግዚአብሔር ክብር በመስጠት ሰባት ቀን አክብሩ፤ በዚህም ቀን ምንም ሥራ አትሥሩ።
ምንም ነውር የሌለባቸውን አንድ ወይፈን፥ አንድ አውራ በግ፥ አንድ ዓመት የሞላቸው ሰባት ተባዕት የበግ ጠቦቶች፥ መዓዛው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ።