ይህንንም ያደረገው እግዚአብሔር ለእስራኤል በሰጠው ሕግ መሠረት፥ ዘወትር ጠዋትና ማታ በሙሉ የሚቃጠለውን መሥዋዕት በመሠዊያው ላይ እንዲያቃጥሉ ነው።
ዘኍል 28:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ለእኔ የሚቀርበውም በእሳት የሚቃጠል የምግብ ቊርባን የሚከተለው ነው፦ በየቀኑ ለሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት አንድ ዓመት የሞላቸውና ምንም ነውር የሌለባቸው ሁለት የበግ ጠቦቶች ይሁኑ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግሞም እንዲህ በላቸው፤ ‘በእሳት ለእግዚአብሔር የምታቀርቡት መሥዋዕት ይህ ነው፤ አንድ ዓመት የሆናቸውንና እንከን የሌለባቸውን ሁለት ተባዕት የበግ ጠቦቶች መደበኛ የሚቃጠል መሥዋዕት በማድረግ በየዕለቱ አቅርቡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህም በላቸው፦ ‘ለጌታ በእሳት የምታቀርቡት ቁርባን ይህ ነው፤ ለዘወትር ለሚቃጠል መሥዋዕት ነውር የሌለባቸውን ሁለት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች ዕለት ዕለት ታቀርባላችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም በላቸው፦ በእሳት ለእግዚአብሔር የምታቀርቡት ቍርባን ይህ ነው፤ ለሚቃጠል መሥዋዕት ነውር የሌለባቸውን ሁለት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች ዕለት ዕለት ታቀርባላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም በላቸው፦ በእሳት ለእግዚአብሔር የምታቀርቡት ቍርባን ይህ ነው፤ ለዘወትር ለሚቃጠል መሥዋዕት ነውር የሌለባቸውን ሁለት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች ዕለት ዕለት ታቀርባላችሁ። |
ይህንንም ያደረገው እግዚአብሔር ለእስራኤል በሰጠው ሕግ መሠረት፥ ዘወትር ጠዋትና ማታ በሙሉ የሚቃጠለውን መሥዋዕት በመሠዊያው ላይ እንዲያቃጥሉ ነው።
ሙሴ ባዘዘው መሠረትም በእያንዳንዱ የበዓል ቀን ማለትም በየሰንበቱ፥ በየወሩ መባቻ፥ በየዓመቱ በሚከበሩ ሦስት በዓላት ማለትም በቂጣ በዓል፥ በመከር በዓልና በዳስ በዓል መሥዋዕት ለእግዚአብሔር ያቀርብ ነበር።
በተጨማሪም ዘወትር በሙሉ የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ በወር መባቻ በዓልና በሌሎችም የተቀደሱ የእግዚአብሔር በዓላት የሚቀርብ መሥዋዕትን በበጎ ፈቃድ ለእግዚአብሔር ከሚቀርበው ከሌላው መሥዋዕት ሁሉ ጋር አቀረቡ።
ሠራዊቱም ቤተ መቅደሱንና አካባቢውን ያረክሳሉ፤ የዘወትር መሥዋዕትም እንዳይቀርብ ያደርጋሉ፤ አጸያፊ የሆነ ርኩስ ነገር በማቆም ጥፋትን ያመጣሉ።
ከዚያ በኋላ አንድ ቅዱስ ሲናገር ሰማሁ፤ ሌላው ቅዱስ ደግሞ ለተናገረው ቅዱስ እንዲህ አለው፦ “እነዚህ በራእዩ የታዩት ነገሮች የሚፈጸሙበት ጊዜ መቼ ነው? ጥፋትን የሚያስከትለው ዐመፅና የዘወትርን መሥዋዕት ተክቶ የሚቈየው እስከ መቼ ነው? ቤተ መቅደሱና የሰማይ ሠራዊት ተላልፈው በመሰጠት ተረግጠው የሚቈዩትስ እስከ መቼ ነው?”
ይህ የሚቃጠል መሥዋዕት በመሆኑ የአሮን ልጆች በሚቃጠለው መሥዋዕት መሠዊያ ላይ ያቃጥሉት፤ ይህ ዐይነቱ መሥዋዕት መዓዛው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ነው።
“ለአሮንና ለልጆቹ የምትሰጣቸው የሥርዓት መመሪያ ይህ ነው፤ የሚቃጠል መሥዋዕት ሌሊቱን ሁሉ በመሠዊያው ላይ እንዲቈይ ተደርጎ እሳቱ ሲነድ ይደር፤
ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! ወደ ቤትኤል ሄዳችሁ ኃጢአት ሥሩ! ወደ ጌልጌላም ሂዱና የበለጠ በደል ፈጽሙ! በየዕለቱ መሥዋዕታችሁን አቅርቡ! በየሦስተኛውም ቀን ዐሥራታችሁን ስጡ።
መዓዛው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘውንም የምግብ ቊርባን በተመሳሳይ ሁኔታ በሰባቱም ቀኖች ውስጥ ታቀርባላችሁ፤ ይህንንም የምታቀርቡት በቀኑ ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕትና የመጠጥ መባ ጋር ተጨማሪ በማድረግ ነው።
ይህን ሁሉ መሥዋዕትና የመጠጥ መባ በቀኑ ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕትና የእህል ቊርባን ጋር ተጨማሪ በማድረግ ታቀርባላችሁ፤ እንስሶቹም ነውር የሌለባቸው መሆናቸውን አረጋግጡ።
ስለ ኃጢአት ስርየትም የሚሆን አንድ ተባዕት ፍየል ታቀርባላችሁ፤ እርሱም ለሕዝቡ የማስተስረይ ሥርዓት በተፈጸመበት ጊዜ ከሚቀርበው ተባዕት ፍየል እንዲሁም ከእህል ቊርባንና ከመጠጥ መባ፥ በየቀኑ ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ጋር ተጨማሪ ሆኖ የሚቀርብ ነው።
ስለ ኃጢአት ስርየትም የሚሆን አንድ ተባዕት ፍየል ታቀርባላችሁ፤ ይህንንም ሁሉ መሥዋዕት የምታቀርቡት በየቀኑ ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት የእህል ቊርባንና የመጠጥ መባ ጋር ተጨማሪ በማድረግ ነው።
ይህንንም ሁሉ መሥዋዕት በየወሩ መጀመሪያ ቀን ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕትና የእህል ቊርባን፥ እንዲሁም በየቀኑ ከሚቀርበው መዓዛው እግዚአብሔርን ደስ ከሚያሰኝ የሚቃጠል መሥዋዕት የእህል ቊርባንና የመጠጥ መባ ጋር ተጨማሪ በማድረግ ታቀርባላችሁ፤ ይህም የምግብ ቊርባን ይሆናል።