ባልዋ ግን “ዛሬ ስለምን ትሄጂአለሽ? ሰንበት ወይም የጨረቃ በዓል የሚከበርበት ጊዜ አይደለም” አላት። እርስዋም “ግድ የለም፤ እንዳልኩህ አድርግ” አለችው፤
ዘኍል 28:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በእያንዳንዱ ወር መጀመሪያ ቀን የሚቃጠል መሥዋዕት ለእግዚአብሔር አቅርቡ፤ ይኸውም ነውር የሌለባቸውን ሁለት ወይፈኖች፥ አንድ አውራ በግ፥ አንድ ዓመት የሞላቸው ሰባት ተባዕት የበግ ጠቦቶች ታቀርባላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘በየወሩ መባቻ እንከን የሌለባቸውን ሁለት ወይፈኖች፣ አንድ አውራ በግ፣ ዓመት የሆናቸውን ሰባት ተባዕት የበግ ጠቦቶችን የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር አቅርቡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በወሩም መባቻ ለጌታ የሚቃጠል መሥዋዕት አቅርቡ፤ ሁለት ወይፈን፥ አንድ አውራ በግ፥ ነውርም የሌለባቸውን ሰባት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች ታቀርባላችሁ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በወሩም መባቻ ለእግዚአሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ታቀርባላችሁ፤ ከላሞች ሁለት፥ አንድ አውራ በግ፥ ነውርም የሌለባቸውን ሰባት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በወሩም መባቻ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ታቀርባላችሁ፤ ሁለት ወይፈን፥ አንድ አውራ በግ፥ ነውርም የሌለባቸውን ሰባት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች፥ |
ባልዋ ግን “ዛሬ ስለምን ትሄጂአለሽ? ሰንበት ወይም የጨረቃ በዓል የሚከበርበት ጊዜ አይደለም” አላት። እርስዋም “ግድ የለም፤ እንዳልኩህ አድርግ” አለችው፤
ከዚህም በኋላ ለጢሮስ ንጉሥ ኪራም የሚከተለውን መልእክት ላከ፤ “አባቴ ንጉሥ ዳዊት ቤተ መንግሥቱን በሠራበት ጊዜ የሊባኖስ ዛፍ እንጨት ትልክለት እንደ ነበር ለእኔም ላክልኝ፤
አሁን እኔ ለአምላኬ ለእግዚአብሔር ስም ቤተ መቅደስን ለመሥራት በመዘጋጀት ላይ ነኝ፤ ይህም ቤተ መቅደስ እኔና ሕዝቤ በእግዚአብሔር ፊት ጣፋጭ ሽታ ያለውን ዕጣን የምናጥንበት የተቀደሰውን ኅብስት ሳናቋርጥ ለእግዚአብሔር የምናቀርብበት፥ በየቀኑ ጠዋትና ማታ፥ እንዲሁም በሰንበቶች፥ በወር መባቻዎችና በሌሎችም በተቀደሱ በዓላት እግዚአብሔር አምላካችንን ለማክበር የሚቃጠለውን መሥዋዕት የምናቀርብበት የተቀደሰ ስፍራ ይሆናል፤ የእስራኤል ሕዝብ ይህን ለዘለዓለም እንዲያደርጉ እግዚአብሔር አዞአል።
ሙሴ ባዘዘው መሠረትም በእያንዳንዱ የበዓል ቀን ማለትም በየሰንበቱ፥ በየወሩ መባቻ፥ በየዓመቱ በሚከበሩ ሦስት በዓላት ማለትም በቂጣ በዓል፥ በመከር በዓልና በዳስ በዓል መሥዋዕት ለእግዚአብሔር ያቀርብ ነበር።
በተጨማሪም ዘወትር በሙሉ የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ በወር መባቻ በዓልና በሌሎችም የተቀደሱ የእግዚአብሔር በዓላት የሚቀርብ መሥዋዕትን በበጎ ፈቃድ ለእግዚአብሔር ከሚቀርበው ከሌላው መሥዋዕት ሁሉ ጋር አቀረቡ።
እንዲሁም ለቤተ መቅደስ አገልግሎት ከዚህ የሚከተሉትን ነገሮች አሟልተን እናቀርባለን፦ ይኸውም የተቀደሰውን ኅብስት፥ በየዕለቱ መቅረብ የሚገባውን የእህል መባ፥ ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚሆኑትን እንስሶች፥ በሰንበት ቀኖች፥ አዲስ ጨረቃ በምትወጣበት ጊዜና በሌሎችም በዓላት የሚቀርበውን፥ ሌላውንም የተቀደሰ መባ ሁሉ፥ ለእስራኤል ሕዝብ ኃጢአት ማስተስረያ መቅረብ የሚገባውንና ለቤተ መቅደሱ የሚያስፈልገውን ሌላውንም ነገር ሁሉ አናስታጒልም።
አንተ መሥዋዕትንና መባን አትፈልግም፤ እንስሶች በመሠዊያ ላይ እንዲቃጠሉ፥ ወይም ለኃጢአት ስርየት የሚሆን መሥዋዕት እንዲቀርብልህ አትጠይቅም፤ በዚህ ፈንታ የአንተን ትእዛዝ በመስማት እንዳገለግልህ አደረግኸኝ።
ከወር መባቻ እስከ ሌላ የወር መባቻ በዓልና ከሰንበት እስከሚቀጥለው ሰንበት ሕዝብ ሁሉ በአዲሲቱ ኢየሩሳሌም ሊሰግዱልኝ ይመጣሉ”፤ ይህን የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።
ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ወደ ውስጠኛው አደባባይ የሚያስገባው ወደ ምሥራቅ አቅጣጫ የሚያመለክተው በር በስድስቱ የሥራ ቀኖች ዝግ መሆን አለበት፤ ነገር ግን በሰንበት ቀንና በየወሩ መባቻ ቀን ይከፈታል።
ከእያንዳንዱ ኰርማና ከእያንዳንዱ የበግ አውራ ጋር አንድ አንድ ኢፍ የእህል መባ ይሁን፤ እንዲሁም ከእያንዳንዱ የበግ ጠቦት ጋር የሚቀርበው መባ መስፍኑ ለመስጠት የፈቀደውን ያኽል ይሁን፤ ከእያንዳንዱም ኢፍ ጋር ሦስት ሊትር የወይራ ዘይት አብሮ ይቅረብ።
ሰውየውም የእንስሳውን የሆድ ዕቃና የኋላ እግሮቹን በውሃ ይጠብ፤ ካህኑም ያን ሁሉ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አድርጎ በማቅረብ በመሠዊያው ላይ በሙሉ ያቃጥለው፤ ይህም ዐይነት በእሳት የሚቃጠል መሥዋዕት መዓዛው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ይሆናል።
ይኸውም ከቀንድ ከብቱ መካከል አንዱን ለሚቃጠል መሥዋዕት ማቅረብ ቢፈልግ ምንም ነውር የሌለበትን ኰርማ መርጦ ያምጣ፤ እርሱም በእግዚአብሔር ፊት የሰመረ መሥዋዕት ይሆንለት ዘንድ በመገናኛው ድንኳን መግቢያ በር በኩል ያቅርበው።
ያም ሰው የእንስሳውን ሆድ ዕቃና የኋላ እግሮቹን በውሃ ይጠብ፤ ካህኑም መሥዋዕቱን በሙሉ በመሠዊያው ላይ ያቃጥለው፤ ይህም የሚቃጠል መሥዋዕት ነው። የዚህ ዐይነቱ መሥዋዕት መዓዛ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ይሆናል።
እናንተ እንዲህ ትላላችሁ፦ “እህላችንን መሸጥ እንድንችል የወር መባቻው በዓል ምነው ቶሎ ባለፈልን! ስንዴ ወደ ገበያ ለመውሰድ ሰንበትም መቼ ያልፍልናል? በዓላቱ ካለፉልን የእህሉን መስፈሪያ አሳንሰን ከፍተኛ ዋጋ እንጠይቃለን፤ በሐሰተኛ ሚዛንም ሕዝቡን እናታልላለን፤
እንዲሁም በደስታ በዓሎቻችሁ፥ ማለት በወር መጀመሪያና በሌሎችም የተወሰኑ በዓሎቻችሁ፥ በሚቃጠል መሥዋዕትና በአንድነት መሥዋዕታችሁ ላይ መለከቶችን ትነፋላችሁ፤ እነርሱም በእግዚአብሔር ፊት ስለ እናንተ አስታዋሾች ይሆናሉ። እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።”
የምግብ ቊርባን አድርጋችሁ የሚቃጠል መሥዋዕት አቅርቡ፤ ይኸውም ነውር የሌለባቸው ሁለት ወይፈኖች፥ አንድ አውራ በግ፥ አንድ ዓመት የሞላቸው ሰባት ተባዕት የበግ ጠቦቶች ታቀርባላችሁ፤
ዳዊትም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ነገ አዲስ ጨረቃ የምትታይበት በዓል ነው፤ እኔም ከንጉሡ ጋር መብላት ይኖርብኛል፤ እስከ ነገ ወዲያ ምሽት ድረስ እንድደበቅ ፍቀድልኝ” አለው።